እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ብ/ቡድኑን ለማሰባሰብ የመንግሥትን ምላሽ እየጠበኩ ነው አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ጉዞን በተመለከተ ከመንግሥት የሚሰጥን ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ካፍ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው መረጃ በኮቪድ 19 የተነሣ የተቋረጠው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 10/2012 በሚካሄዱ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች የሚቀጥል መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህን የካፍ ውሳኔ ተከትሎ ከሀትሪክ ጥያቄ የቀረበላቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንደተናገሩት

“ባለፉት 2 ወራት ከመንግሥት አካላት ጥሩ ግንኙነት ፈጥረናል፡፡ በቡድኑ ዙሪያ ያለው ሂደት ተመልክተው የሚሰጡት ምላሽ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን በኛ በኩል አሰልጣኝም ብሔራዊ ቡድን ይኖረናል፡፡ ውድድር ባይኖርም ብሔራዊ ቡድን መኖሩ የግድ ይላል፡፡ የመን ለእስያ ዋንጫ ያለፈችው ውድድር ኖሮ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “የጤና ሚኒስቴር ዶክተሮች ቅዳሜ ዕለት በነበረው ውይይት ላይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ደረጃው የት ድረስ እንደሚደርስም እናውቅም ሲሉ ተናግረዋል ይህም ሁኔታው ከበድ እያለ እየመጣ እንደሆነ ያሳያል በኛም ሀገር በቀን 1 ሺ ሰው በኮቪድ 19 እየተያዘ ነው፤ መንግሥት ህይወት ይቀድማል በማለቱ አሁን የሚሰጠንን ምላሽ እንጠብቃለን”

 

ያሉት ፕሬዚዳንቱ አቶ ኢሳያስ “ከኒጀር ጋር ላለብን ጨዋታ 2 ወር ከ15 ቀን ይቀረናል፡፡ በቀጣይ 15 ቀን ውስጥ አንድ ውሣኔ ላይ ከደረስን ቀጣዮቹን 60 ቀናት እንጠቀማለን፡፡ መንግሥት ከዘጋ ዘጋ ነው ህይወት ነው የሚቀድመው መልካሙን በመመኘት ግን የሚጠበቅብንን ስራ እንሰራለን” ሲሉ ለሀትሪክ አስረድተዋል፡፡

“በጋራና በሀገር ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ ሰው የለም፡፡ አንድ ፕሮፌሰር ግብጾችን ሲመክር ኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ ፖለቲካ አለ ብላችሁ እንዳትሸወዱና ጦርነት እንዳታውጁ … ይሄን ትቶ በጋራ በሀገር ጉዳይ ለመሰባሰብ አንድ ቀን አይፈጅባቸውም ሲል ተናግሯል… በሀገር ጉዳይ በብሔራዊ ቡድን ዙሪያ ሁሉም አንድ ነው፡፡ በሀገር ውክልና በኩል ኢትዮጵያዊያን በአንድ አቋም የሚታሙ አይደለም፡፡ በሽታው ይወገድ እንጂ ችግሩ ይጥፋ እንጂ ሀገራዊ የእግር ኳስ ውክልና ላይ ሁሉም አንድ ነው፡፡ ፌደሬሽኑም በቀጣይ ይህን የእግር ኳስ አንድነት ይመራል”

ሲሉ ለሀትሪክ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport