“እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ከራሱ አንፃር የሚጠቅመውን እንጂ ሰው የሚያመውን እየሰራ አይደለም” አቶ መንግስቱ ሳሳሞ (የሊግ ኮሚቴ ሥ/አ አባልና የሲዳማ ቡና ስራ አስኪያጅ)

“እናንተ ጋዜጠኞች ለምትፈልጉትና ለከፈላችሁ ታወራላችሁ፤ ለማትወዱትና ላልከፈላችሁ አታወሩም”
“እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ከራሱ አንፃር የሚጠቅመውን እንጂ ሰው የሚያመውን እየሰራ አይደለም”
አቶ መንግስቱ ሳሳሞ

ጅማ አባጅፋር ከባህር ዳር ከተማ ጋር ተጫውቶ 1ለ0 ተሸንፏል፤ከጨዋታው በላይና ከተመዘገበው ውጤት ባሻገር አነጋጋሪ የነበረው የመመዝገቢያ ክፍያ ካልከፈሉ 7 ክለቦች መሀል አንዱ መሆኑ ነው፡፡ ስድስት ክለቦች የመመዝገቢያ 870 ሺህ ብር አልከፈላችሁምና ታግዳችኋል ሲባሉ ስድስቱ ከፈሉ…ጅማ አባጅፋርስ? የአዲሱ የሊግ ኮሚቴ ውሳኔ ምን ይሆን? የሚለው አጓጊ ነበር፡፡ ጨዋታው ሊጀመር ሰዓታት ሲቀሩት የሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ የሊግ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወደሆኑት አቶ መንግሥቱ ሳሳሞ ጋር ደወለ….. በሠላምታ የተጀመረው ቃለ-ምልልስ በከባድ ስም ማጥፋትና ሚና ባልለየ የአቶ መንግሥቱ ዘለፋ ተጠናቀቀ እንዲህ አዘጋጅተነዋል፡፡

ሀትሪክ፡- …አቶ መንግሥቱ ሳሳሞ ኖዎት…?
መንግሥቱ፡- …አዎ ነኝ…፤
ሀትሪክ፡- …ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ እባላለሁ…፤
መንግሥቱ፡- …ሠላም ነው ጠፋህኮ…?…የጠፋ ድምፅ ከየት ተገኘ…?
ሀትሪክ፡- …የወዳጅ ድምፅ አይጠፋምኮ…ትንሽ ቢዚ ሆኜ ነው…፤
መንግሥቱ፡- …/ሳቅ/ ሠላም ነኝ ምን እግር ጣለህ…?
ሀትሪክ፡ …ያልከፈሉ ክለቦች ይታገዳሉ…የሚለው ሕግ ከምር የወጣ ነው…?…6ቱ ከፍለው ሰባተኛው ጅማ አባጅፋር ሳይከፍል ሊጫወት ነው እንዴ…?
መንግሥቱ፡- …/ቆጣ ብለው/…ምንም ጥያቄ አያስነሳም…እኔ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነኝ…አንድ ነገር ላስረዳህ…ባለመክፈሉ የሚሰረዝ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ አልነበረም፤ሚዲያዎች የራሣችሁም አጀንዳ ነበራችሁ…ነገር ግን አጀንዳውን የማልቀበለው ነው…አካሄዱ እንዲስተካከል እንዲለወጥ እንጂ አንዱን የመጉዳት አይደለም…የከፈሉ ክለቦች ከ120-200 ሺህ ብር እዳ ነበረባቸው አሟልተው የከፈሉ አልነበሩም፤9ኙ ክለቦችም ማለቴ ነው…እኔ የስራ አስፈፃሚ አባል ነኝ በጊዜው ክፍያው እንዲፈፀም ሁሉም ክለቦች የመንግሥት በጀት ያለባቸው ናቸው፡፡ በዚያ ላይ አንዱ ከፍሎ ሌላው እንዳይከፍል የተደረገ ሳይሆን ፌዴሬሽኑ በሚመራበት ዘመን በራስ አካውንት ስለሚገባ ገንዘቡን እየከፈለ መክፈል ያለባቸውን እያስከፈለ የአገሪቱ ክለቦች ከው ድድሩ እንዳይወጡ እያደረገ ሠላም እየፈጠረ ያመጣበት እንጂ አንዱን አኑሮ ሌላውን የማጥፋት ጉዳይ አይደለም፡፡
ሀትሪክ፡- በጁፒተር ሆቴል በነበ ረው የግምገማ መድረክ ላይኮ 9ኙ አልከ ፈላችሁምና ታግዳችኋል ብላችኋል፤ይሄ እኮ እውነት ነው…ሚዲያ ታዲያ የራሱ አጀንዳ ነበረው እንዴት ይባላል?
መንግሥቱ፡- ተብሏል እኔም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነኝ…የናንተን ችግር ልንገራችሁ…ወልቂጤ ላይ ነፍስ ጠፍቷል ተብሎ ሲነገር አላወራችሁም…እናንተ ስታወሩ የነበረው…ገንዘብ ስላለመክፈልና ስለ ክለብ መታገድ ነው…ግምገማው ላይ ግን ትልቁ ጉዳይ እርሱ ነው? ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት የተነገረው ትልቅ ጉዳይ አልነበረም? ማን ጥሩ ሰራ? ማን መጥፎ ሰራ? የትኛው ክለብ ችግር ነበረበት ተብሎ አልተነሣም? ለምን ይሄንን ለማውራት አልቻላችሁም…ሁሉንም ሚዲያ ሰምቻለሁ…አንዱም አላቀረበም…እናንተ ገንዘብ ተቀብላችሁ ለምትወዱት የምታውሩ ናችሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …አቶ መንግሥቱ…ይሄኮ ስድ ብና ስም ማጥፋት ነው?
መንግሥቱ፡- …ክፉ ናችሁ…ክፋታችሁ ምን እንደሆነ ታውቁላችሁ…?…እናንተ ጋዜጠኞች ለምትፈልጉትና ለከፈላችሁ ታወራላችሁ…፤…ለማትወዱትና ላልከፈላችሁ አታወሩም…የኢትዮጵያ ፕሪሚ የር ሊግ ችግሩ ገንዘብና እገዳ ነው እንዴ…?…ነው ትልቁ ችግር በዘርና በማንነት ሲደረስ የነበረው አደጋ ነው…?…እርሱን ለማስወገድ ምን አወራችሁ…?…ፍፁም ሠላማዊ ነው ትላላችሁ…ሰው የቆሰለበትና የደማበትን ግን አታወሩም…አንድም ግምገማው ላይ የነበረ እውነትን ሳታወሩ…እነ እገሌ ታገዱ የሚለው ነበር አጀንዳችሁ…በቃ ልንገርህ አይታገዱም…የሚታገዱበትም ምክንያትም የለም…ገንዘብ ከተፈለገ ማክሰኞ ድረስ ይከፈላል…በቃ…፡፡
ሀትሪክ፡- …የናንተም ራስ ምታትማ ነበረኮ…አገድን ያላችሁት እናንተ…ዜናው ስናወራ የምትቆጡት እናንተ…ሚዲያው ምን ያድርግ ታዲያ…?
መንግሥቱ፡- …ግልፅ አድርገን አውር ተናል…ያንን ዝጋና ይህንን አውራ ያለው ማነው…?…ዋናው ችግር ጎሰኝነት እና ሜዳ ላይ የሚገጥመው ችግር እንጂ…የ800ና የ700 ሺህ ብር ጉዳይ አይደለም…ለምን እርሱ ላይ ትንጠለጠላላችሁ…?…ሚዲያ ከሆንክ ለምን ትንጠለጠላለህ…?…ይሄንን እያመመኝ ነው የምናገረው…፡፡
ሀትሪክ፡- …አቶ መንግሥቱ የምንጠ ለጠልበት ጉዳይ የምንመርጠውማ እኛ ነንኮ…?
መንግሥቱ፡- …እኔ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነኝ…ጅማ አባ ጅፋር አልከፈ ለም… ማክሰኞ ይከፍላል…፤…እንዲጫወት ወስነናል፤…ምን የሚያም ነገር አለው…? (ቃለ- ምልልሱ የተሰራው እሁድ እለት ነው)
ሀትሪክ፡- …ሚዲያንማ አያመውም…ነገር ግን ውሳኔው በራሱ ዜና ነው…?
መንግሥቱ፡- …አዎ ለእናንተማ ምርጥ ዜና ነው…በሁለተኛው ዙር አደጋ ሊፈጠር ይችላል ጥንቃቄ ያስፈልጋል ተብሎ መወራት ሲኖርበት የናንተ ወሬ ገንዘብ ነው ዋናው ጉዳይ…የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አንድነትና ሠላም ነው ለምን እርሱ ላይ አታተኩሩም? መቼም ቢሆን የማወራው በዚህ ቶን ነው…ማንንም ሚዲያ በዚህ ቶን ነው የማናግረው…የሊግ ኮሚቴ አባል ነኝ ይጫወታሉ በቃኮ ወስነናል…
ሀትሪክ፡- …ተስማማን እኮ መደጋገሙ አይጠቅምም አቶ መንግሥቱ…?
መንግሥቱ፡- …ካልከፈላችሁ ትታገዳላ ችሁ ያልነው ለዳኛ የምንከፍለው ገንዘብ ስላጣን ነው…መታገዱ ነው እንዴ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግር? ችግር የነበረው በሃይማኖትና በዘር በጎሳ የነበረው አድማና ድርጊቱ ነው፤ የሚዲያው ትልቅ ችግር ግን ገንዘብ ነው እገሌ ታግዷል…ተጨዋች ማዘዋወር አይችልም የምትሉት እሱ ነው እንዴ ራስ ምታታችን? ተጨዋች አዘዋውረንስ ምን አመጣን? የቱን ብሔራዊ ቡድን ፈጠርን በዚህ ቶን ለኢትዮጵያ ህዝብ ገልጬ ስራውን እተወዋለሁ…በጣም እያመመኝ ነው የምናገረው…የኢትዮጵያ ሚዲያ አንዱን በማጥፋት አንዱን በማልማት ላይ የሚሰራ ነው…እንደ ሀገር ነው ሊያመን የሚገባው…ትኩረት መስጠት ያለብን የዳኛ ገንዘብ መክፈል አለመከፈል ላይ አይደለም…የሀገሪቱ ስፖርት ወዴት እየሄደ ነው? በሚለው ላይ ነው መነጋገር አለብን፡፡
ሀትሪክ፡- …ሀትሪክ ጋዜጣ ላይ እሰራ ዋለሁ?
መንግሥቱ፡- …በደንብ ስራው ይሄ የኔ አጀንዳ ነው…በደንብ ስራው…ሁሉም ይነጋገርበት…እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ከራሱ አንፃር የሚጠቅመውን እንጂ ሰው የሚያመውን ጉዳይ እየሰራ አይደለም፤አገር የሚያመውን ሳይሆን እንደራሱ ጥቅም የሚያመውን የሚያወራ ህዝብ ያለበት ሀገር ነው…አንድ ብሔራዊ ቡድን ማውጣት ያቃተን ሀገር ውስጥ ሁሉም በየራሱ ፍላጎት እየነዳን መኖር የለብንም…በቃ፡፡
ሀትሪክ፡- …ጨርሻለሁ…አቶ መንግሥ ቱ ለሁሉም አመሰግናለሁ
መንግሥቱ፡- …በቃ ቻው…

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport