የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ነገ ማለዳ ለንባብ ስትበቃ ምን ምን ይዛ ይሆን? በሀገር ውስጥ ተወዳጅነትን ባተረፈላትና ብዙ ተከታታዮች ባሉት THE BIG iNTERVIEW አምዷ ወደ ሊጉ መሪነት ከረዥም ጊዜ በሃላ የተመለሰው የቅ.ጊዮርጊስ ቁልፍ ተጨዋች ጋዲሳ መብራቴ በክለቡና በራሱ ዙርያ ብዙ ሊለን እንግዳ ሆኖ ቀርባል።
ጋዲሳ ስለ ግል ህይወቱ፣ስለ ክለቡና ቀደም ሲል ክለቡ ከድቶት ስለነበረው ውጤት ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀትሪክ ተንፍሷል፤”ዘንድሮ ያለፍትን ሁለት አመታት ጉዞ በውጤት የምናካክስበት አመት ይሆናል” ሲል የደጋፊውን ተስፋ የሚመልስ አስተያየት ሰጥቷልና የነገ ማለዳ ሀትሪክ እንዳታመልጥዎ።ከጋዲሳ በተጨማረ “አሁንም ሲዳማዊ ነኝ” በማለት የሚናገረው አዲስ ግደይ በእግር ኲስ አጀማመሩና ዕድገቱ ዙርያ ብዙ ብሎናል የነገ ማለዳዋን ሀትሪክ ይጠብቁ።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም በህትመት ሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፕርምዬር ሊግ የመጡትን አዲስ ፈራሚዎች የአርሰናሉ ፓብሎ ማሪና የማን.ዩናትዱን ብሩኖ ፈርናንዴስን ማንነት ታስቃኘናለች፤ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱም ተጫዋቾች ለአዲሱ ክለባቸው የሰጡትን ያልተሰማና ያልተነበቡ ቃለ-ምልልሶችን ይዛ ቀርባለችና የነገ ማለዳ ቀጠርዎ ከሀትሪክ ጋር ይሁን።መች ይሄ ብቻ የሊቨርፑልና ሌሎች ዘገባዎችንም ሀትሪክ ይዛ ነገ ማለዳ እጅዎ ትገባለችና ይጠብቃት።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ ከፍተኛ መሻሻል ባሳየውና በአጭር ጊዜ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋ hatricksport.net አዳዲስና ያልተሰሙ ትኩስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
መች ይሄ ብቻ ሀትሪክ በቅርቡ ከጋዜጣና ዌብሳይቷ በተጨማሪ በመፅሔትም አንባቢዎቿ ጋር ለመድረስ መስናዶዋን አጠናቃለች።
ሀትሪክን በባለ ቀለም ጋዜጣ
ሀትሪክን በድረ-ገፅ(ዌብሳይት)
በቅርቡ ደግሞ ሀትሪክን ደረጃውን በጠበቀ መፅሔት ይኮሞኩሟታል፤በቅርቡ ይጠብቁን።
ሀትሪክ የስፖርት መፅሔትን በቅርብ ቀን!!
We Feed Spirt!! ስፖርትን እንመግባለን!!
አስተያየት ይስጡ