እኔ ለወልዋሎ በሚል መሪ ቃል ዛሬ በአዲግራት ሩጫ ተካሄደ

 

እኔ ለወልዋሎ በሚል መሪ ቃል አዲግራት ላይ የአራት ኪሎ ሜትር ሩጫ ዛሬ ተካሂዷል።

 

ዛሬ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲን ክለብ የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት ታሰቦ የተደረገው ይሀ ሩጫ በሁሉም እድሜ አንድ ላይ በአራት ኪሎሜትር ውድድሩ ተደርጓል። በርካታ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሩጫ ከውድድር ባለፈም ለህብረተሰቡ የመዝናኛ መንገድ ነበር።

ከአንድአመት ከስድስት ወር በኋላ ወደ ሜዳው በመመለስ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በ15ኛው ሳምንት ከወልቂጤ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ደጋፊዎች ክለባቸው ለማየት እንደጓጉ በውድድሩ በጉልህ ሲንፀባረቅ የነበረ ጉዳይ ሆኖ አልፋል። የውድድሪ አሸናፊዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

 

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team