“እረፍቴን በግሌ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ነው የማሳለፈው።”ዘላለም ኢሳያስ /ሀዋሳ ከተማ/

👉👉 “ከኔ ይልቅ ጓደኛዬ ሲያገባ ነው ደስ የሚለኝ።”

👉👉 “እረፍቴን በግሌ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ነው የማሳለፈው።”

👉👉 “በሽታውን እግዚአብሔር እስኪያስወግድልን አስገዳጅ ነገሮች ካልገጠሙን በስተቀር ከቤታችን ባንወጣ ጥሩ ነው።”

👉👉 “ለኔ አራአያዎች የምላቸው ከሀገር ውስጥ አሸነፊ ግርማ እና ሙልጌታ ምህረት ናቸው።”

በትንሽ የግብ ልዩነት በሚጠናቀቁበት ጨዋታዎች እና ጥቂት የግብ እድሎች በሚፈጠርበት ሊጋችን የግሉን ችሎታ በመጠቀም በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አመቻችቶ በማቀበል ለቡድኑ የማሸነፊያ ሌላ አማራጭ በመፈለግ ከሚታትሩ ተጫዋቾች በግንባር ቀደምትነት በሊጉ ይጠቀሳል የሀዋሳ ከተማው አማካይ ዘላለም ኢሳያስ። ተጫዋቹ ስለ እግር ኳስ ህይወቱ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርጓል።

ዘላለም ኢሳያስ ስለ እግርኳስ ህይወቱ ይናገራል።


በቅድሚያ ውድ ጊዜህን ሰውተህ ይህንን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ስለፈቀድክ በሐትሪክ ስፖርት ድረገፅ ስም እናመሰግናለን።

እኔም አመሰግናለሁ።

ስለ ትውልድህ እና የአግር ኳስ ህይወቱ አጀማመርህ እንጀምር እና እናውራ

ተወልጄ ያደኩት ሀዋሳ ነው ያው የእግር ኳስ ህይወትን የጀመርኩት በፕሮጀክት ደረጃ ነው። በክለብ ደረጃ መጫወት የጀመርኩት 2005 በቀድሞ አጠራሩ በብሄራዊ ሊግ ለወልቂጤ ከተማ ነው። ከዛ 2007 ወደ ደቡብ ፖሊስ አምርቼ ለሁለት አመታት ቆይታ አድርጊያለው በመቀጠል 2009 ወደ ድሬዳዋ ተጉዤ ለሁለት አመት ቆይታ ካደረኩ በኋላ 2011 በድጋሚ ወደ ደቡብ ፖሊስ ተመልሼ ተጫወትኩ ዘንድሮ ደግሞ እንደምታውቀው ለሀዋሳ ከተማ እየተጫወትኩ እገኛለሁ። ከ20 አመት በታች ለብሄራዊ ቡድንም መጫወት ችያለው የአሰልጣኝ ግርማ የነበረው ቡድን ውስጥ።

በሊጉ ለጎል የሚሆኑ ኳሶች አመቻችተው ከሚያቀብሉ ተጫዋቾች አንተ ግንባር ቀደም ነክ ለዚህ ልዩ ክህሎትህ ምስጢሩ ምንድነው?

እግር ኳስ ተሰጥኦ ነው ሁሉም የየራሱ ችሎታ ነው ያለው የተለየ ስራ ሰርቼ አደለም ያደኩበት ነገር ስለሆነ ነው። ከኔ ይልቅ ጓደኛዬ ሲያገባ ነው ደስ የሚለኝ። እኔ ለጎል አመቻችቼ የምሰጠው ኳስ ጎል ሲሆኑ በጣም ደስ ይለኛል። ወደ ልምምድ ስገባም ትኩረት አድርጌ ምሰራው አብረውኝ ለሚጫወቱ ቅድሚያ በመስጠት ከማግባት ይልቅ ኳስ አመቻችቼ ማቀበል ነው ይህን ክህሎትም ያዳበርኩት ከዛ የመነጨ ነው።

በአለማች እንዲሁም በሀገራችን በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ሊጋችን ተቋርጠዋል የእረፍት ጊዜህን በምን እያሳለፍክ ትገኛለክ በተጨማሪም ለህብረተሰቡ የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ።

እረፍቴን በግሌ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ነው ማሳለፈው። ያው እንደ ቡድን እንደምትሰራው ባይሆንም ማለት ነው። ምክንያቱም እግር ኳስ የግሩፕ ስራ ስለሆነ። ቤት ውስጥ እንቅስቃሴ እያደረኩ እገኛለው። ያለመድነው የሕይወት ዘይቤ ስለሆነ ትንሽ ያስቸግራል። ያለ እንቅስቃሴ መቆየት ከባድ ነው ቢሆንም ሊጉ እስከሚጀመር በግል መንቀሳቀስ ብቸኛው አማራጭ ነው። ኮሮና ቫይረስ በአለም ደረጃ በጣም አስጊ በሽታ ነው፤ በርካታ የሰው ህይወትም እየቀጠፈ ነው እግዚአብሔር ይመስገን እኛ ሀገር እንደተፈራው አልተስፋፋም። ነገር ግን ይህ በሽታ በሀገር ደረጃ ከተስፋፋ መቋቋም አንችልም ምክንያቱም በእውቀትም ሆነ በኢኮኖሚ ከኛ የተሻሉ ሀገራት ከአቅማቸው በላይ ሆኗል። እነሱ ከቤት አትውጡ ሲባሉ ብዙ ነገሮች ተመቻችቶላቸው ነው፤ እኛም ጋር ችግሮችን ለመቅረፍ ከተለያዩ ቦታዎች ድጋፍ እየቸደረጉ ነው ይሁን እንጂ በቂ ነው ብዬ አላስብም በዚም ሆነ በዛ አስከፊ ችግር ሳይመጣብን በቻልነው አቅም መረባረብ አለብን። በሽታውን እግዚአብሔር እስኪያስወግድልን አስገዳጅ ነገሮች ካልገጠሙን በስተቀር ከቤታችን ባንወጣ ጥሩ ነው።

እግር ኳስ ተጫዋች እንድሆን ከሀገራችንም ከውጭ አርአያዬ ናቸው የምትላቸው ተጫዋቾች እና ተጫዋች ብሆን ለዚህ ክለብ ብጫወት ምኞቴ ነበር የምትለው

ለኔ አራአያዎች የምላቸው ከሀገር ውስጥ አሸነፊ ግርማ እና ሙልጌታ ምህረት ናቸው። የአጨዋወት ዘይቤያቸው በጣም ነው የሚመቸኝ እና የምወድላቸው። ከውጪ ደግሞ ፋብሪጋስ ነው። በእግር ኳስ ውስጥ መግለፅ ከምችለው በላይ የምወደው ሜሲን ነው። ካቅም በላይ ስለሚሆን እሱ ከሰው ልጅ አእምሮ በላይ ነው ለኔ። ከልጅነቴ ጀምሮ እመኝ የነበረው ለሀዋሳ ከተማ መጫወት ነበር እሱም ተሳክቶልኛል። በሁኔታዎች አለመመቻቸት ማድረግ ያለብኝን ነገር እያደረኩ ነው ብዬ አላምንም ከዚህ የተሻለ ነገር ለመስራት እመኛለው። በምወደው ክለብ ውስጥ ነው ያለሁት፤ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ።

በሀገራችን እና በውጪ ሀገር ተጫዋቾች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

የእምነት ጉዳይ ነው፤ ለምሳሌ እኔ እና አንድ የውጪ ሀገር ተጫዋች አንድ ክለብ ብንሆን በክህሎትም ባቅምም የተሻልክም ሆነህ ብዙ ጊዜ አሰልጣኞች ቅድሚያ የሚሰጡት ለሱ ይሆናል እንጂ ከኛ ከጥቂቶቹ በስተቀር የሰፋ ልዩነት አለን ብዬ አላምንም።

ለብሔራዊ ቡድን ደረጃ ለመጫወት ተመራጭ ለመሆን ምን ታስባለህ?

ለብሔራዊ ቡድን መጫወት የማይፈልግ የለም ብሔራዊ ቡድን ለመጫወት በተሻለ መልኩ ጠንክሬ መስራት እንዳለብኝ አምናለው። ያንንም ከፈጣሪ ጋር አሳካለው።

የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ባንተ እይታ?

ሊጋችን አዳዲስ ተጫዋቾች በማፍለቅ ረገድ ደካማ ነው ይባላል ይህም እውነት ነው። የተተኪዎች ችግር ግን የለብንም እኛ የወጣንባቸው ፕሮጀክቶች በአሁኑ ስአት ጠፍታዋል። እነሱ ለተጫዋቾች የመውጫ መንገድ ነበሩ እነሱ ከሌሉ ደግሞ ተተኪ ማፍራት ከባድ ነው። ለወጣቶች ቦታ መሰጠት አለበት ሲባል ግን ነባር ተጫዋች ከአዳጊዎቹ በማቀላቀል ማጫወት ነው ያለብን።

እግርኳስ ተጫዋች ባትሆን ምን ትሆን ነበር?

እኔ እንጃ አስቤ አላቅም ምክንያቱም ከልጅነቴ ጀምሮ ኳስ እየተጫወኩ ስላደኩ። ኳስ ተጫውቼ ወደ ቤት ስመለስ አባቴ በጣም ነበር የሚገርፈኝ እንደዛም ሆኖም ግን ከኳስ አላራቀኝም።

ላንተ እዚህ ደረጃ መድረስ አስተዋፅኦ ያላቸው ሰዎች?

ብዙ ናቸው ከፕሮጀክት ስነሳ ዮሴፍ ገብረወልድ (ወፍዬ)፣ ያሬድ ገመቹ እንደ አባት ወንድም አድርጎ ያሳደገኝ አሰልጣኝ ነው። በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ዘላለም ሽፍራው ጥሩ የሚባል ጊዜ ወዳሳለፍኩበት ድሬዳዋ ወስዶ በወጣቶች እምነት ያለው ጥሩ አሰልጣኝ ስለነበር የተሻልኩ እንድሆን አድርጎኛል። ወደ ደቡብ ፖሊስ ስመለስ ደግሞ ገብረክርቶስ ቢራራ ትንሽ አኩራፊ ስለነበርኩ በብዙ መልኩ አግዘውኛል።

ስለነበረን ቆይታ በሐትሪክ ድረገፅ ስም በድጋሚ በጣም እናመሰግናለን።

እኔም በጣም አመሰግናለሁ።