ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ ትልቁን ጨዋታ ይመራል !

የአፍሪካ የክለቦች ውድድር ኳከነገ ጀምሮ መካሄዳቸውን ሲጀምሩ ተጠባቂ መርሀ ግብሮችን የሚስተናገዱበት ይሆናል ።

ኢትዮጵያዊው ስኬታማ ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ ወይሳም የፊታችን ማክሰኞ በአፍሪካ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በግብፁ ፒራሚድ ክለብ እና በጊኒው ሆሮያ ክለብ መካከል የሚካሄደውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት እንደሚመራ ለማወቅ ተችሏል ።

ባምላክ ተሰማ ከዚህ ቀደም ሀያ አምስት የሚጠጉ የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በበላይነት መምራት ሲችል ከሁለት ዓመታት በፊት በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዛማሊክ እና በሞሮኮው ቤርኬን መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት መምራቱ የቅርብ ትውስታ ነው ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor