የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቡድንን ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ያሳለፉት ኢንስትራክተር ሠዉነት ቢሻው ወደ ጋቦን ተጋዙ።ኢንስትራክተሩ ወደ ጋቦን የተጒዙት በአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ሲሆን ድርጅቱ አሰልጣኙ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ግምት ዉስጥ በመክተት ሙሉ ወጪያቸው ተሸፋፍኖላቸዉ ዛሬ ጠዋት ወደ ጋቦን አምርተዋል ። ኢንስትራክተሩ ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸው በፊት ከሀትሪክ ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ማክሰኞ ይጠብቁን።
አስተያየት ይስጡ