መነሻ ገጽ ሪፖርት ኢትዮጵያ ቡና ከተከታታይ ሽንፈቶች በኃላ ወደ እሸናፊነት ተመልሷል
ሪፖርትወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡና ከተከታታይ ሽንፈቶች በኃላ ወደ እሸናፊነት ተመልሷል

አጋራ
አጋራ

በ18ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪይምየር ትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም ላይ የተካሄደው የወልዋሎና የኢትዮጵያ ቡና ጨወታ በእንግዶቹ ኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል።ቡናማዎቹን ከ5 ተከታታይ ሽንፈት በኃላ 3 ነጥብ ያስገኘችውን ብቸኛ ግብ እማኑኤል ዮውሃንስ በ49ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል።

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለን ከገጠመው ስብስብ ዳንኤል እድሃኖምን በብርሃኑ ቦጋለ ቀይረው ወደ ሜዳ ገብተዋል።ኢትዮጵያ ቡናም በተመሳሳይ በ16ኛው ሳምንት ከድሬዳዋ ጋር ከተጫወተው ምርጥ 11 3 ቅያሬዎችን ማለትም በተካልኝ ደጀኔ፣ቶማስ ስምረቱ ና ሱሌይማን ሎክዋ ምትክ ኣህመድ ረሺድ፣ሻባኒ እልሁሴን ና ሄኖክ ካሳሁን ቀይረው ገብተዋል።በኣንጻራዊነት ወልዋሎዎች ተሽለው በታዩበት የመጀመርያው 45 በሁለቱም መስመር በኤፍሬም እሻሞ ና በእንየው ካሳሁን አማካኝነት እድሎቹን ሲፈጥሩ ነበር።የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ በ5ኛው ደቂቃ በሁለተኛው ዙር በተለየ ሚና ከእጥቂ ጀርባ እየተሰለፈ ያለው ፕሪንስ ሰርቪንሆ በግምት ከ25 ሜትር እክርሮ የመታው ካስ ግብ ጠባቂው ወንድወሰን እሸናፊ እድኖበታል።ጫና መፍጠራቸውን የቀጠሉት ወልዋሎዎች በ19ኛው ደቂቃ ሃይሉ ገ/ትንሳኤ ኤፍሬም እሻሞ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ራሱ ኤፍሬም ቢመታውም የግቡ ኣግዳሚ መልሶበታል። በመጀመርያዎቹ 20 ደቂቃዎች ላይ ወደ ጨዋታው መግባት የተቸገሩት ኢትዮጵያ ቡና ቀስ በቀስ ወደ የጨዋታውን ፍጥነት መስተካከል ችለዋል።ሄኖክ ካሳሁን በግምት ከ20 ሜትር የመታው ኳስ ኣብዱላዚዝ ኬይታ በጥሩ ሁኔታ የመለሰበት ኳስ የቡናዎቹ የመጀመርያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ነበር።ወልዋሎዎች በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ቡናን ፍጹም ቅጣት ሳጥን ጋር ቢደርሱም የሜዳው መጨረሻ ክፍል ሲደርሱ የነበራቸው አለመናበብ የጠራ የግብ እድል እንዳይፈጥሩ አድርጓቸዋል።

ሁለተኛው እጋማሽ ላይ ሃይሉ ገብረትንሳኤን በእያሱ ታምሩ ቀይረው የገቡት ኢትዮጵያ ቡና ኳሱን ከመጀመሪያው 45 በተሻለ መልኩ ተቆጣጥረው መጫወት ችለዋል፤የዚህም ውጤት በ48ኛው ደቂቃ እቡበከር ነስሩ ከግራ መስመር ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ይዞት የገባውን ኳስ መሬት ለመሬት ወደ ውስጥ ሲያሻማው ሻባኒ መትቶት የወልዋሎ ተከላካዮች መልሰውት የተገኘውን ኳስ እማኑኤል ዮውሃንስ ቡናን መሪ ማድረግ ችሏል።ከጎሉ ሁለት ደቂቃ በኃላ እስራት ቱንጆ ከአማኑኤል ጎበና የነጠቀውን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ቢመታውም አብዱላዚዝ ኬይታ እድኖበታል።ሁለተኛው እጋማሽ መጀመርያ ላይ ራችሞንድ ኦዶንጎን በአብዱራህማን ፋሱይኒ የቀየሩት ወልዋሎ የጠበቁትን ለውጥ ማየት እልቻሉም።

ቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎዎች በኤፍሬም እሻሞ ና ተቀይሮ በገባው ሰመረ ካህሳይ አማካኝነት ሙከራዎቹን ቢያደርጉም እቻ ሚያደርጋቸውን ግብ ማግኘት ሳይችሉ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና እሸናፊነት ተጠናቋል።

ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ከእምስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኃላ ወደ እሸናፊነት እንዲመለሱ አድርጓቸዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...