በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ስሙ ከብዙ ክለቦች ጋር እየተነሳ የነበረው ታፈሰ ሰለሞን በመጨረሻ ማረፍያውን ኢትዮጵያ ቡናን አድርጓል።
የካሳዬን አጨዋወት ለመተግበር ያግዛሉ የተባሉ ተጨዋቾችን በማስፈረም ላይ ሚገኙት ቡናዎች ታፈሰ ሰለሞንን በማስፈረም የመሃል ሜዳቸውን እያጠናከሩ ይገኛሉ።

ላለፋት ሁለት ዓመታት በሃዋሳ ከተማ ቆይታ ያደረገው ታፈሰ ሰለሞን በሁለት ዓመት ውል ኢትዮጵያ ቡና መቀላቀሉን ተከትሎ ካሳዬን በክረምቱ ያስፈረመው ሥስተኛ የመሃል ሜዳ ተጨዋች ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ