ኳስ መጫወት እሚችል ግብ ጠባቂ ሲያፈላልጉ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡና በረከት አማረን ከወልዋሎ ማስፈረም ችለዋል።
በ2009 ወልዋሎ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገው ወጣቱ ግብ ጠባቂ በረከት አማረ የህክምና ምርመራ በማድረግ ለሁለት ዓመት ሚያቆየውን ውል ፈርሟል።
በ2009 የከፍተኛ ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኖ የተመረጠው በረከት ባሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀዋሚ ተሰላፊነቱን በአብዱላዚዝ ኬይታ ተነጥቆ አብዛኛውን ጊዜ ተቀያሪ ወንበር ላይ አሳልፏል።
በተጨማሪም ቡናዎች የአቤል ከበደን ዝውውር በማጠናቀቅ የክረምቱ ፈራሚዎቻቸውን ቁጥር አስር አድርሰዋል።
አስተያየት ይስጡ