መነሻ ገጽ Mikkeller Aarhus / cross championship IAAF | ኢትዮጵያ በዴንማርክ አርሁስ በተደረገው አገር አቋራጭ ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነች
Mikkeller Aarhus / cross championshipሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስሀገር አቋራጭዜናዎች

IAAF | ኢትዮጵያ በዴንማርክ አርሁስ በተደረገው አገር አቋራጭ ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነች

አጋራ
አጋራ

በፈረንጆቹ ቀን አቆጣጠር ማርች 30 ለአንድ ቀን በተከናወነው ውደድር ኢትዮጵያን አትሌቶች ጎልተው በመውጣት የውድድሩ ኩራት መሆነ ችለዋል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ 5 የወርቅ 3 የብርና 3 የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ 11 ሜዳሊያ በማግኘት ነው በበላይነት ማጠናቀቅ የቻለችው።

ኬኒያ በ 2 ወርቅ 3 ብርና 3 ነሃስ ሜዳሊያ ሁለተኛ ወጥታለች።

ውድድሮቹ በአዋቂ ወንዶችና ሴቶች የ10 ኪሎ ሜትር፣ በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር፣ በወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትርና በ8 ኪሎ ሜትር ድብልቅ የዱላ ቅብብል ተካሂዷል።

በዚህም በአዋቂ ወንዶች 10 ኪሎ ሜትር የኡጋንዳዎቹ ጆሺዋ ቺፕቴጌና ጃኮብ ኪፒሊሞ ተከታትለው ሲገቡ ኬኒያዊው ጂኦፈሪ ኮሞሮሮ ሶስተኛ ወጥቷል።

በውድድሩ የአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ሰለሞን ባረጋ አምስተኛ ወጥቷል።

በአዋቂ ሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ሄለን ኦብሪ ከኬንያ ቀዳሚ ሆና ስትገባ ደራ ዲዳና ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል።

ከሀያ አመት በታች ወጣት ወንዶች 8 ኪሎሜትር ሚልኬሳ መንገሻ ቀዳሚ ሲሆን ታደሰ ወርቁ ሁለተኛ ሆኗል።ከ20 አመት በታች ሴቶች 6 ኪሎሜትር ቤትሪሲት ቺሌት ከኬንያ ቀዳሚ ስትሆን አለሚቱ ታሪኩ ሁለተኛ ጽጌ ገብረሰላም ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በ8 ኪሎ ሜትር ድብልቅ ውድድር ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆናለች።

ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት በኡጋንዳ ርዕሰ መዲና ካምፓላ በተካሄደው 42ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በ4 የወርቅ፣ በ4 የብርና በ1 የነሐስ በድምሩ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

ኬንያ በሻምፒዮናው 4 የወርቅ፣ 5 የብርና 3 የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አሸናፊ መሆኗ አይዘነጋም።

የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ከ1965 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አገራት እየተካሄደ የሚገኝ ውድድር ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ሻምፒዮና እየተካፈለች ትገኛለች።

በዴንማርኳ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ባከናወነው ውድድር በርካታ ኢትዮጵያን በውድድሩ ቦታ ላይ በመገኘት አትሌቶቻችን አበረታተዋል።




አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...