By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: አፄዎቹ በሜዳቸው ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል
Share
Notification Show More
Latest News
March 13, 2026
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ
ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ
ዜናዎች ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች መቐለ 70 እንደርታ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችፋሲል ከተማሪፖርት

አፄዎቹ በሜዳቸው ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል

hatricksport team
hatricksport team 8 years ago
Share
SHARE

በጎንደር  ፋሲለደስ ስታድየም በተደረገው የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ፋሲል ከነማ በመሀመድ ናስር ብቸኛ ጎል አርባምንጭን 1ለ0 በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል፡፡

አፄዎቹ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና 3ለ2 ከተሸነፈዉ የቡድን ስብስብ ዉስጥ አንድ ተጫዋች ለውጥ ያደረጉ ሲሆን በቡናዉ ጨዋታ በቀይ ካርድ የወጣው ራምኬሎክ ቦታ ናትናኤል ጋንቹላ  በመተካት የተለመደውን 4_2_3_1 አሰላለፍ ተጠቅመው ገብተዋል፡፡

ከወትሮ በተለየ መልኩ የደጋፊ ቁጥር ቀንሶ በታየበት በዚህ ጨዋታ አፄዎቹ የመጀመሪያውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሙሉ ብልጫ ወስደው መጫወት የቻሉ ሲሆን ከ5ኛው ደቂቃ ጀምሮ ነበር ወደ ተጋጣሚ የጎል ክልል ውስጥ መድረስ የቻሉት፡፡ ዘንድሮ ቡድኑን የተቀላቀለው መሀመድ ናስር 2 የአርባምንጭ ተከላካዮችን አታሎ በማለፍ ያሻማውን ኳስ ኤፍሬም አለሙ መትቶት ግብ ጠባቂው በቀላሉ ያዳነበት ሲሆን በደቂቃዎች ልዩነት ናትናኤል ጋንቹላ ከርቀት አክሮ የመታው ኳስ በጎሉ አግዳሚ የወጣችው ኳስ በመጀመሪዎቹ 10 ደቂቃዎች አፄዎቹ ያደረጓቸው ለጎል የቀረቡ ሙከራዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ 
ጎል ለማግኘት ይበልጥ ተጭነው የተጫወቱት ፋሲሎች ኤፍሬም አለሙና ኤርሚያስ ሃይሉ በጥሩ ቅብብል ያሻገሯትን ኳስ በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው መሀመድ ናስር አክርሮ በመምታት አፄዎቹን መሪ ማድረግ የምትችል ኳስ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ይች ጎል ለመሀመድ ናስር ቡና ላይ ካስመዘገባት ጎል ቀጥሎ ክለቡን ከተቀላቀለ በኃላ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ሁና ተመዝግባለታለች፡፡
በአንፃሩ የአፄዎቹ ተጋጣሚ አርባ ምንጭ ከተማዎች በመጀመሪያው አጋማሽ የመጀመሪያ ሙከራ ለማድረግ 35 ያህል ደቂቃዎን የፈጀባቸው ሲሆን 7 ቁጥሩ እንዳለ ከበደ ከርቀት መትቶ በግቡ ቋሚ የወጣችው ኳስ በአዞዎቹ በኩል ብቸኛ የጎል ዕድል ሁና በመመዝገብ የመጀመሪያው አጋማሽ በፋሲል መሪነት ሊጠናቀቅ ችላል፡፡
አዞዎቹ ከእረፍት መልስ መጠነኛ የጨዋታ መሻሻል አድርገው ቢገቡም ኳስን መሐል ሜዳዉ ላይ ከማንሸራሸር ዉጭ ይህ ነዉ ሊባል የሚችል የኳስ ሙከራ ሲያደርጉ አልተስተዋሉም፡፡ በ47ኛዉ ደቂቃ የፊት አጥቂው ፀጋዬ አበራ ከፍፁም ቅጣት ምት መምቻዉ አቅራቢያ መትቷት ወደ ዉጭ ከወጣችዉ ኳስ በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል የጎል ሙከራ አላደረጉም፡፡ በተመሳሳይም ፋሲሎች የመሐል አማካዩ ያሳር ሙገርዋ የግል ክህሎቱን በመጠቀም በርካታ የአርባምንጭ ተጫዋቾችን አታሎ በማለፍ ለናትናኤል ጋንቹላ አሻግሮለት ሞክሮ ከመስመር ላይ ከተመለሰችዉ ኳስ በስተቀር ያን ያህል ለጎል የቀረቡ ሙከራዎች ሲያደርጉ አልተስተዋሉም፡፡ 

በተደጋጋሚ በዳኛ ሲቆራረጥ በነበረውና ሃይል በተቀላቀለበት በዚህ ጨዋታ በፋሲል በኩል1 ቢጫ በአርባምንጭ ደግሞ 3 ቢጫና 1 ቀይ ካርድ የተመዘገቡ ሲሆን ከመጀመሪያው አንፃር የተቀዛቀዘ እና በፋዉሎች የታጀበ ጨዋታ ሁኖ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠርበት በአፄዎቹ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት 

- ማሰታውቂያ -

ምንተስኖት ጌጡ-ፋሲል ከተማ

“ጨዋታው ጥሩ የሚባል ሲሆን በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ በሙሉ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በመዉሰድ ጎል ያስቆጠርን ሲሆን የጎል መጠኑን ማስፋት የምንችልበት አጋጣሚ ሳንጠቀምበት ቀርተናል፡፡ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግን ዉጤት ይዞ ለመዉጣት ካለን ፍላጓት የተነሳ ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ ያደረግን ሲሆን ከ70 ደቂቃ በኃላ ወደ 4-5-1 ቅርጻችንን በመቀየር መከላከሉ ላይ አመዝነናል፡፡ የመጀመሪያው ዙርን በአሸናፊነት ማጠናቀቃችን ያስደሰተኝ ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተጎዱብንና የተቀጡ ተጫዋቾች ተመልሰዉና በመጀመሪያው ዙር የነበሩንን ክፍተት ቀርፈን ጠንካራ ሁነን ለመቅረብ እንሰራለን፡፡”

አሰልጣኝ እዮብ ማለ-አርባምንጭ ከተማ

“ጨዋታዎ በጣም ጥሩ ነበር። ባጠቃላይ ጥሩ ተንቀሳቅሰናል። በቀጣይ ሁለተኛ ዙር ጥሩ ቡድን ይዘን እንቀርባለን።በልጆቼ እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ”

You Might Also Like

March 13, 2026

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article ሪፖርት | ሲዳማ ቡና ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
Next Article ድሬ ከተማ ከተከታታዬ ሽንፈት በኃላ ወደ ድል ሲመለስ አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር ነጥብ ተጋርተዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎችዜናዎችአርባምንጭ ከተማ

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

ቴዎድሮስ ታከለ By ቴዎድሮስ ታከለ 1 week ago
“የኢት.ቡናን ችግር ለማስወገድ አስተዳደራዊ ሳይሆን የሜዳ ላይ ችግሮችን አስቀድሞ መፍታት ይገባል” “በአምስት ዓመት የብ/ቡድን ቆይታዬ ከ30 በላይ አሰልጣኞች ተፈራርቀውብኛል” ዕድሉ ደረጄ (የቀድሞ የኢት.ቡና ተጨዋችና አሰልጣኝ)
“የሳላህዲን ሰይድና የእኔ ለኮከብ ተጨዋችነት ምርጫ እጩ ውስጥ አለመካተታችን አግራሞትን ፈጥሮብኛል፤ ለመሆኑ መራጬ አካል ማን ነው?” ጌታነህ ከበደ /ደደቢት/
ዋና ዳኛ ማርታ መለሰ በካፍ ጥሪ ተደርጎላታል
የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የምድብ ድልድል በአክሲዮን ማህበር ምስረታ ወቅት በእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ይለያል::
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?