አጫጭር የሀገር ውስጥ የዝውውር መረጃዎች(ጭምጭምታዎች) !

 

ሀትሪክ ስፖርት የሀገር ውስጥ የዝውውር መረጃዎችን ተመልክቶ ይጠናቀቃሉ ተብሎ በስፋት የሚጠበቁ እና በጭምጭምታ ደረጃ ያሉ የዝውውር መረጃዎችን የምናቀርብልዎ ይሆናል ።

– ኮከቦቹን ባልተጠበቀ መልኩ እያጡ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ከአምበላቸው አዲስ ግደይ ጋር መለያየታቸው ሲታወቅ በቀጣይ ከመሀል ሜዳው ዳዊት ተፈራ ( ኦዚል ) ጋራ ሊለያዩ እንደሚችል ተሰምቷል ።

ዳዊት ተፈራ በቀጣይ ማረፊያውን የአምና ሻምፒዮኖቹ መቐለ 70 እንደርታ ሊሆን እንደሚችል በጭምጭምታ ረገድ ተሰምቷል ።

– ኢትዮጵያ ቡና የኮከቦቹን ውል በማራዘም ላይ ሲገኝ የሲዳማ ቡናውን የመስመር ተጫዋች ዮናታን ዮሐንስን ዝውውር እንደሚያጠናቅቁ ይጠበቃል ።

– የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ በዝውውሩ ስማቸው በስፋት ከማይነሱ ክለቦች ውስጥ ሆነው ሲገኙ በመጪው ቀናት በሊጉ በአማካይ ስፍራ ላይ አስደናቂ ብቃተቸውን ካሳዩ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነውን የመከላካያውን ፍሬው ሰለሞን ( ጣቁሩ ) የግላቸው እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።

መቐለ 70 እንደርታ ከ ፍሬው ሰለሞን በተጨማሪ በጣናው ሞገድ ደማቅ የውድድር ዓመት ማሳለፍ የቻለውን ፍጹም ዓለሙን እንደሚያስፈርሙ ይጠበቃል ።

 

– ከአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ( ሞሪንሆ ) ጋር የተለያዩት መከላከያዎች በቀጣይ ፓውሎስ ጌታቸው ( ማንጎን ) የክለቡ አሰልጣኝ አድርገው እንደሚሾሙ ይጠበቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor