አዳማ ከተማ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ !

 

በአሰልጣኝ አስቻለው ሀይለ ሚካኤል የሚመሩት አዳማ ከተማዎች በርካታ ተጫዋቻቸውን ቢነጠቁም አሰልጣኝ አስቻለው ሀይለ ሚካኤል ወጣት ተጫዋቾችን ጨምሮ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየተስማሙ ይገኛሉ ።

በዛሬው ዕለትም በሊጉ ልምድ ያለውን ግብ ጠባቂ ታሪክ ጌትነትን ለማስፈረም መስማማታቸው ለማወቅ ተችሏል ።

ታሪክ ጌትነት በአሸናፊ በቀለ በቀጣይ ዓመት የሚሰለጥነውን ሀድያ ሆሳዕናን በመልቀቅ ነው ለአዳማ ከተማ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ይፋ የሆነው ።

ታሪክ ጌትነት በደደቢት ፣ ወላይታ ድቻ ፣ አዳማ ከተማ ከዚህ ቀደም በመጫወት ሲያሳልፍ ከግብ ጠባቂያቸው ጃኮ ፔንዞ ጋር ለመለያየት ለተቃረቡት አዳማ ከተማዎች ዳግም ጥሩ ብቃቱን እንደሚያሳይ ይጠበቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor