አዳማ ከተማ ደመወዛችን ተቀነሰ ባሉ 9 ተጨዋቾች ተከሠሠ

 

የ50ሺ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ገደብን የሚደነግግ ደንብ መውጣቱ እያወዛገበ ባለበት አዳማ ከተማ ከህጉ መውጣት በፊት ውል የተዋዋላቸውን ተጨዋቾች ደመወዝ በመቀነስ 34 ሺ ብር መክፈሉ ተቃውሞ አስነስቶበታል፡፡

.ወደ 5 ወር የሚጠጋ ደመወዝ ያልከፈለው አዳማ ከተማ የ2 ወር ደመወዝ ሰሞኑን የከፈለ ሲሆን ሁሉንም በ34 ሺ ብር ደመወዝ መክፈሉ ዳዋ ሁቴሳ ከነአን ማርክነህ ምኞት ደበበ ሱሌይማን መሃመድ በረከት ደስታ ቡልቻ ሹራ ብሩክ ቃልቦሬን ጨምሮ በ9 ተጨዋቾች መከሰሱ ታውቋል፡፡ ተጨዋቾቹ ዛሬ ክሳቸውን ለፌዴሬሽን ያስገቡ ሲሆን የክለቡ አዲሱ ስራ አስኪያጅ አቶ ገመቹ መኮንን ስልክ ቢደወልላቸውም ቴክስት ቢደረግላቸውም አለመመለሳቸው የክለቡን አቋም ማወቅ አልቻልንም፡፡ የፌዴሬሽኑ ጊዜያዊ ዋና ጸሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ግን “ከህጉ በፊት የነበረው ውል መጣስ የለበትም..በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ከሌለ በተናጠል የሚወሰኑ ውሳኔዎችም ተቀባይነት የለውም” ሲሉ የፌዴሬሽኑን አቋም ገልጸዋል::

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport