አዳማ ከተማ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

 

ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር ከተለያዩ በኋላ ከበርካታ ተጫዋቾቻቸው ጋር እየተለያዩ የቆዩት አዳማ ከተማዎች የፊት መስመር አጥቂያቸውን ውል ማራዘማቸው ታውቋል ።

በሊጉ የፊት መስመር ስፍራ ላይ ልምድ ካላቸው መካከል አንዱ የሆነው ሚካኤል ጆርጅ በአዳማ ከተማ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት መስማማቱን ለማወቅ ተችሏል ።

ቁመተ መለሎው እና በአካል ብቃት ጥንካሬው የሚታወቀው ሚካኤል ጆርጅ ሊጉ ዳግም ሲጀምር ቡድኑን በአምበልነት እንደሚመራ ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች ።

ሚካኤል ጆርጅ ከዚህ ቀደም በሊጉ ሻምፒዮን ደደቢትን ጨምሮ በሙገር ሲሚንቶ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ዳሽን ቢራ እንዲሁም አውስኮድ የተሳካ ጊዜን ማሳለፉ ይታወሳል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor