አዳማ ከተማዎች ወደ ልምምድ ተመልሰዋል

 

ደሞዝ አልተከፈለንም በማለት ልምምዳቸውን አቁመው የነበሩት አዳማ ከተማዎች ወደ ልምምድ ተመልሰዋል።

የክለቡ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ደሞዝ አልተከፈለንም በማለት ልምምድ ያቆሙ ሲሆን ያለ ምንም ዝግጅት ድሬዳዋ መግጠማቸውም አይዘነጋምተ። ነገር ግን ዛሬ የ1 ወር ደሞዝ ተከፍሏቸው ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታው በፏላ ወደ ልምምድ መመለሳቸው ተሰምቷል። ሆኖም ግን የሀምሌ እና የናህሴ ወር ደሞዝ መከፈል አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት የአዳማ ተጫዋቾች በዚህ ሳምንት ወደ ሀዋሳ አቅንተው ሲዳማን በሚገጥሙበት ጨዋታ አመራሮቹ ቅሬታ ውስጥ ከመሆናቸው አኳያ ውጤቱን እንዳያበላሹ ተፈርቷል ይላል ሀትሪክ ያገኘችው መረጃ።

 

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor