አዲሴ ካሳ ከሀዋሳ ጋር ሊለያዩ ይሆን

አዲሴ ካሳ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ሊለያይ የሚችል ሌላኛው የሊጉ አሰልጣኛ ሊሆን ይችላል።

 

ሀዋሳ ከተማ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ከተለያየ በኋላ ከ2011 ጀምሮ ሲያሰለጥኑ የቆዩት አሰልጣኙ አዲሴ ካሳ እያስመዘገቡ ባሉት ደካማ ውጤት ከቡድኑ ጋር ሊለያዩ እንደሚችሉ ከታማኝ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ። በሌሎች አስልጣኞች የማይዘወተረው በወጣቶች እምነት ጥለው ከታች በማሳደግ ዋናው ቡድን ላይ የሚጠቀሙት አሰልጣኙ ቀጣይ እጣ ፈንታቸው ምን ይሆን የሚለው ተጠባቂ ሲያደረገው። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሙልጌታ ምህረት ከቡድኑ ጋር ስሙ እየተያያዘ ይገኛል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor