“አንደኛውን ዙር በመሪነት ማጠናቀቃችን የሊጉን ዋንጫ እንድናነሳ ትልቅ ጉልበት ይሆነናል” አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪምየር
ሊግ የአንደኛ ዙርን በመሪነት
አጠናቋል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ
ተሳትፎው መሪ ሊሆን የቻለው ተከታዮቹን
ቡድኖች መቐለ 70 እንደርታና ፋሲል ከነማን
በሁለት እና በሶስት ነጥቦች ልዩነት በመብለጥ
ሲሆን ከአዳማ ከተማ ጋር አድርጎት የነበረውን
የመጨረሻ ጨዋታ 0ለ0 ተለያየ እንጂ ያን
ጨዋታ አሸንፎ ቢሆን ኖሮ ተከታዩን ቡድን
በአራት ነጥብ ልዩነት የሚበልጥበት ዕድል
ይፈጠርለት ነበር፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእዚህ
የመጀመሪያው ዙር የውድድር ተሳትፎው
ለስኬት እንዲበቃና መሪም ሊሆን እንዲችል
በአጥቂ ስፍራ ላይ የሚገኙት አቤል ያለው እና
ጌታነህ ከበደ የነበራቸው ጥምረት በብዙዎች
ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት እንዲሰጣቸው ያደረገ
ሲሆን ሁለቱ ተጨዋቾችም በጋራ ለክለቡ
13 ጎሎችን ሊያስቆጥሩለትም ችለዋል፤
የክለቡን የአንደኛው ዙር ጉዞ እና አጠቃላይ
ውድድሩ ምን መልክ እንደነበረው እንደዚሁም
ደግሞ በሁለተኛው ዙር ላይ ክለባቸው በምን
መልኩ እንደሚቀርብ የክለቡን የአጥቂ ስፍራ
ተጨዋች አቤል ያለውን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ
አናግሮታል፤ ተጨዋቹም ምላሹን በሚከተለው
መልኩ ሰጥቷል፡፡

ስለ ቅ/ጊዮርጊስ የአንደኛው ዙር ጉዞ?

“የሊጉ ውድድር ላይ አጀማመራችን ጥሩ
አልነበረም፤ በኋላ ግን እየተሻሻልን መጣንና
በቅርብ የነጥብ ልዩነት ቢሆንም መሪ ሆነን
የመጀመሪያ ዙርን ልናጠናቅቅ ችለናል፤ ከዛ
ውጪ ማለት የምፈልገው ደግሞ ዘንድሮ
ከሜዳ ውጪ ማሸነፍ ለሁላችንም ቡድኖች
ከብዶን ነበር ያም ሆኖ ግን ይሄ ችግር አሁን
ላይ እየተቀረፈ የመጣበትና መቀራረብም
ስለተቻለ የውድድር ጉዞአችንን እንደአጠቃላይ
በመሪነት ለማጠናቀቅ መቻላችን ለእኛ በጥሩ
መልኩ የሚገለፅ ነው”፡፡

በመጀመሪያው ዙር ፈታኝ ስለሆነባቸው
ቡድን?

“ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሰቲ ነዋ!
እነሱ ላይ ቀድመን ግብ በማስቆጠር አሸነፍ
ናቸው እንጂ በጣም ነበር ያስቸገሩን፤ በእያን
ዳንዱ እንቅስቃሴ አይቆሙም ስቃይም ነበር
የሆኑብን”፡፡

ቅ/ጊዮርጊስ በሁለተኛው ዙር በምን መልኩ
እንደሚቀርብ?

“የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎአችን
ላይ አሁን ካለን ብቃት በተሻለ መልኩ ብዙ
ነገርን ማድረግ እንችል ነበር፤ ተከታያችንንም
ቡድን በተወሰነ መልኩ በነጥብ መራቅም
ይገባን ነበር፤ ያም ሆኖ ግን የኳስ ነገር
ሆነና ያን ሳናደርግ ቀረን የሁለተኛው ዙር
ላይ ግን በርካታ ጨዋታዎቻችንን በሜዳችን
የምናደርግበት እድሉ ስላለ ለእዛ ጠንክረን
ሰርተን መጥተን አሁን ካስመዘገብነው ውጤት
በላይ እንደሚኖረን በጣሙን እርግጠኛ ነኝ”፡፡

የትኞቹ ክለቦች ጠንካራ ተፎካካሪያቸው
እንደሚሆኑ?

“ለዋንጫው ባለቤትነት ከሆነ መቐለ
70 እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና
ናቸው፤ ከዛ ውጪ ከሆነ ግን ሁሉም ቡድን
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመጫወት ሲመጣ
ጠንካራ ሆኖ ነው የሚመጣው”፡፡

የሊጉን ውድድር እስካሁን ከስፖርታዊ
ጨዋነት አንፃር ስትመዝነው

“የእኛ ክለብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቡድኖች
እስካሁን እያደረጓቸው ባሉት የሜዳቸውም ሆነ
የሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎች ከስፖርታዊ
ጨዋነት ጋር በተያያዘ በጣም ጥሩ ጥሩ
ነገሮችን እየተመለከትን ነው፤ ጥቂት የሚባሉ
ችግሮችም ናቸው እየታዩ ያሉት፤ እነዚህ
ችግሮች ደግሞ መቀረፍ የሚችሉ ስለሆኑ
ከፍተኛ ትኩረት ለሚሰጠው ክለቦችም
ለሻምፒዮናነት እና ከሊጉ ላለመውረድ
ለሚጫወቱበት የሁለተኛው ዙር ውድድር
ላይ ከወዲሁ በቂ ክትትል የሚደረግበት
ነገር ተፈጥሮ የዘንድሮ ውድድር በሰላም
የሚጠናቀቅበት እና አሸናፊው ቡድንም
ከኳስ በወጣ ነገር ሳይሆን በላቡና በላቡ ብቻ
ሻምፒዮና የሚሆንበትን ነገር እንድንመለከት
ከፍተኛ ምኞቴ ነው”፡፡

በውድድሩ ስለነበራቸው ጠንካራ እና
ደካማ ጎን?

“ሊጉ ሲጀመር አካባቢ ጥሩ የነበረው
ጎናችን መከላከሉ ላይ ነበር፤ ያኔ ጎል አናገባም
ነበር፤ ወደ በኋላ ላይ ደግሞ ጎል ማግባት
ጀመርን፤ ክፍተታችን ደግሞ አንድአንዴ
የምንዘናጋው ነገር አለና ይሄን ችግር በፍጥነት
ልንቀረፈው ይገባል”፡፡

ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረጉት የሊጉ ጨዋታ
እንደተጠበቁት ያለመሆን ችግር እና ደጋፊዎቻቸውን
በውጤት አለማስደሰት?

“ከእነሱ ጋር የነበረንን ጨዋታ አሸንፈን
መሪነታችንን እንደምናጠናክርና ከተከታዩ
ቡድንም ጋር ያለንን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት
እንደምናሰፋ በደጋፊዎቻችን ዘንድ በጣም
ተጠብቆብን ነበር፤ የእኛም ምኞት ጨዋታውን
አሸንፎ በመውጣት መራቅ ነበር፤ ያም
ሆኖ ግን ያ ተጠባቂነታችን በሜዳ ውስጥ
ጫና ውስጥ እንድንገባ ስላደረገን እና በኳስ
የሚያጋጥምም ነገር ስለሆነ ያን ልናሳካው
ሳንችል ቀርተናል፤ የአዳማ ከተማ ጋር
ያደረግነው አይነት ጨዋታ ሁለተኛው ዙር
ላይም ሊያጋጥመን ስለሚችል ለእኛ ከወዲሁ
ትምህርት የሆነን ነው፤ ይህን ችግር ቀርፈን
መጥተን ቀጣዩ ዙር ላይ በስኬታማነታችን
እና በመሪነታችን እንቀጥልበታለን”፡፡

እንደ ቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ተጨዋችነትህ በአንደኛው ዙር ላይ ምርጥ ተጨዋች ነበርክ ማለት ይቻላል…?

“እኔ እንደዛ አልልም፤ ሁሌም ክለቤን
ነው ከፊት የማስቀድመው፤ ከዚህ በፊትም
ነግሬካለው፤ ለክለቤ ውጤት ማማር ብቻም
ነው ኳስን የምጫወተው”፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ካደረጋቸው የመጀመ
ሪያው ዙር ጨዋታዎች አስቆጪው?

“አስቆጪዎቹ ጨዋታዎች በሜዳችን ከሽረ
እንደስላሴና ከአዳማ ከተማ ጋር እንደዚሁም
ደግሞ ከሜዳችን ውጪ ከፋሲል ከነማ ጋር
ያደረግናቸው ናቸው፤ በተለይ ከፋሲል
ጋር ስንጫወት ግጥሚያው እነሱ ሜዳ ላይ
እንደመደረጉ እና ከሜዳ ውጪ ስትጫወት
ደግሞ በጫና ውስጥ ሆነ ስለምትጫወት ያንን
በጥሩ ሁኔታ ተቋቁመን እና ጥሩ ተጫውተንም
ነው በድል አድራጊነት ግጥሚያውን
ልናጠናቅቅ በተቃረብንበት ሰዓት ተገቢ ባልሆነ
የዳኝነት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የፍፁም ቅጣት
ምት ተሰጥቶብን ነጥብን ልንጋራ የቻልነው፤
የዳኝነት ውሳኔ ተገቢ ላይሆን ቢችል በእግር
ኳስ ሜዳ ላይ ያለ እና የሚጋጥም ነገር ነው፤
ስለዚህ ከዚህ ውጪ ሌላ የምለው ነገር ብዙም
የለኝም ”፡፡

ከአዳማ ከተማ ጋር በነበራችሁ ጨዋታ
ለውጤት ማጣታችሁ ብዙዎቹ አሰልጣኙን
ተጠያቂ አድርገዋል፤ አንተም እንደእነሱ ነው
የምትለው?

“በፍፁም፤ እኔ እንደዛ አልልም፤ ምክን
ያቱም በእሱ ተመርተን ያሸነፍናቸው ጨዋታ
ዎችም አሉና ውጤት ያጣነው አስቀድመን
ያሰላነው ስሌት ስለነበር እንጂ በእሱ ችግር
አይደለም፤ አሁን ከእነሱ ጋር ደግመን ብን
ጫወት ጨዋታውን እርግጠኛ ሆኜ የምነግ
ርህ እናሸንፋቸዋለን”፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሌም ምን አይነት እግር
ኳስ ቢጫወት በጣም ደስ ይልሃል?

“ቡድናችን የራሱ የሆነ የአጨዋወት
ስልትና ታክቲክ አለው፤ ያም ቀጥተኛ የሆነ
እግር ኳስ ጨዋታ ነው፤ ይሄ አጨዋወትም
እንደእኛ ላሉ አይነት ፈጣን አጥቂዎች
ጎሎችን እንድናስቆጥርለት ስለሚረዳ እና ለእ
ኔም ስለሚመቸኝ ይሄ ነው የእኔ ምርጫዬ”፡፡

በመጀመሪያው ዙር 7 ግብ አስቆጥረሃል፤
በሁለተኛው ዙርስ ስንት ግብ ይኖርሃል?

“ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ ያንሳ
እንጂ እኔ በቀጣዩ ዙር ስለማስቆጥረው የጎል
ብዛት ፈፅሞ የምጨነቅ አይነት ተጨዋች አይ
ደለውም፤ ስለዚህም አሁን እያሰብኩ ያለሁት
ለቡድኔ ውጤት ማማማር በምን መልኩ ነው
ቡድናችንን የምጠቅመው በሚለው ላይ ብቻ
ነው”፡፡

በፕሪምየር ሊጉ አንደኛው ዙር ከተቃራኒ
ቡድን ተጨዋቾች ለአንተ ምርጡ?

“የኢትዮጵያ ቡናው አማኑኤል ዩሃንስ
ሜዳ ላይ በሚያሳየው ጥሩ ጨዋታም ሆነ
ታታሪነት ለእኔ ቀዳሚው ምርጫዬ ነው”፡፡

የፕሪምየር ሊጉን የአንደኛው ዙር በቀዳሚነት ማጠናቀቃችሁ ለእናንተ በጣም ጥሩ ነው?

“እንዴ በሚገባ ነዋ! አሁን 50 ፐርሰንት
ጨርሰናል ማለት ነው፤ ሁለተኛ ዙርን እንደ
አዲስ ነው የምንጀምረው፤ ስለዚህም ይሄ አሁን
የያዝነው ውጤት ለቀጣይ ጊዜ ጉዞአችን በጣም
የሚጠቅመን ነው፡፡ የሊጉን ዋንጫ እንድናነሳም
ትልቅ ጉልበት ነው የሚሆነን”

የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ወደየት ያመራል?

“እሱማ የታወቀ ነው፤ ምን ጥርጥርስ
አለው፤ ሳንጃው ዋንጫውን ያነሳል”፡፡

ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች?

“በሜዳችንም ሆነ ከሜዳችን ውጪ
ስንጫወት እነሱ ሁሌም ቢሆን ለእኛ ተጨማሪ
ኃይሎች ናቸው፤ ለአንደኛው ዙር ድጋፋቸውም
ከፍተኛ ምስጋና አለኝ፤ የሁለተኛው ዙር ላይ
ደግሞ ይሄ ክለብ ባልተለመደ መልኩ ላለፉት
ሁለት ዓመታት ዋንጫ ያጣ ከመሆኑ አንፃር
ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ከፍተኛ ድጋፍና
በቅርብም የአይዞ ባይነትና የአብሮነትንም
ሁኔታዎች ስለሚፈልግ በዛ መልኩ እንድንደገፍ
መልእ ክቴን አስተላልፋለው”፡፡

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website