አንበሳ ቢራ አዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ስፖንሰር ለማድረግ ተስማማ

ኤርሚያስ ስፖርትስ ማኔጅመንት ባደረገው ጥረት ዩናይትድ ቤቬሬጅስ አዳማ ከተማ እግር ኳስ ቡድንን ለአምስት ተከታታይ አመታት የማልያ ላይ ስፖንሰር ለማድረግ በዛሬው እለት በቃል ደረጃ ስምምነት ፈፅመዋል።

ዩናይትድ ቤቬሬጅስ ለአዳማ ከተማ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን አዳማ ከተማ
እግር ኳስ ክለብ ደግሞ በሚጠቀምባቸው ማልያዎችና በተለያዮ የስፖርት በእቃዎችና ዝግጅቶች ላይ የዩናይትድ ቤቬሬጅስ ምርቶችነን የሚያስተዋውቅ ይሆናል።

ሀትሪክ ስፖርት ተጨማሪ መረጃዎችን የስምምነት ፊርማ በሚፈረምበት ቀን በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የምናሳውቅ ይሆናል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team