አብዱሰላም አማን እና ስሑል ሽረ በስምምነት ተለያይተዋል

ባለፈው አመት ቡድኑን ተቀላቅሎ የነበረው አብዱሰላም አማን ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀምን በመቅጠር በሁለተኛው ዙር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ በተጫዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፉ ያሉት ስሑል ስረዎች አያስፈልጉኝም ከሚሏቸው ተጫዋቾች ጋርም እየተለያዩ ሲሆን። ከዚህ ቀደም ከመድሀኔ ብርሀኔ ጋር መለያየታቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ከመስመር ተከላካያቸው አብዱሰላም አማን ጋር ተለያይተዋል። ተጫዋቹ ለደደቢት፣ኢትዮጵያ ቡና፣ ዳሽን ቢራ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ መጫወት ችሏል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor