ለቻን 2020 ማጣሪያ የፊታችን መስከረም 11 በትግራይ ስታድየም የሩዋንዳ አቻውን ሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአራት ተጨዋቾች ጥሪ አድርጓል።ጥሪ የተደረገላቸው ተጨዋቾች አስቻለው ግርማ፣ፍቃዱ ዓለሙ፣መሳይ ፓውሎስ ና ኤፍሬም አለሙ ሲሆኑ ዛሬ ወደ መቐለ የሚጓዘውን ስብስብ ይቀላቀላሉ።
የሃዋሳ ከተማው ተከላካይ መሳይ ፓውሎስ እና ባህርዳር ከተማን የተቀላቀለው ኤፍሬም አለሙ ለመጀመርያ ጊዜ የብሄራዊ ቡድን ጥሪ ሲደረግላቸው የመከላከያው አጥቂ ፍቃዱ ዓለሙ ከዚህ በፊት ከጅቡቲ ጋር በነበረው ጨዋታ ጥሪ ተደርጎለት መጫወት ችሏል።
አስተያየት ይስጡ