አስተያየት | ጅማ አባጅፋር 2-1 ድሬዳዋ ከተማ

👉 “ቡድኔ ቀይ ካርድ ከተመለከተ ቦኃላ ክፍተቶች ነበሩብን”የሱፍ ዓሊ(የጅማ አባጅፋር ምክትል አሰልጣኝ)

👉”ራሳችን በሳትናቸው ኳሶች ዋጋ ከፍለናል”ፍስሀ ጥዑመልሳን (የድሬዳዋ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኝ)


ቡድኔ ቀይ ካርድ ከተመለከተ ቦኃላ ክፍተቶች ነበረበት” (የጅማ አባጅፋር ምክትል አሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ)

ስለ ጨዋታው

የዛሬ ጨዋታ እንዳያችሁት ከሆነ ኳስን ይዘን ነው የተጫወትነው። እነሱ በሚጣሉ ኳሶች አድርገው ነው እሚጫወቱት። ተጭነን ነበር ስንጫወት የነበርነው ይቺን ኣጋጣሚ ተጠቅመው ግብ ጠባቂው ባዳለጠው ምክንያት ቀይ ካርድ ካየ በኋላ ነበር ትንሽ የኛ ክፍተት የነበረው። ግብ እስክናገባ ኣጥቂዎችን ኣልቀየርንም ጎል ካገባን በኃላ አጥቂ ቀይረን ለመከላከል ተከላካይ አስገብተናል።

ባልተለመደ መልኩ ዛሬ የተከላካይ ክፍላቹ ትንሽ የመረበሽ ነገር ነበር ከቀይ ካርዱም ተዳምሮ ይሄ ነገር እንዴት ነው

ይሄ ነገር እንዳየሀው ከሆነ ማለት ነው። አጨዋወታችን በሁለት ፊድ ባክ እየወጡ ነበር ሲጫወቱ የነበሩት። አንደኛው የውጭ ተጫዋች ነው። በድግግሞሽ ሲሰራ ነው እሱን ከነ መላኩ ጋር ማስተካከል የሚቻለው። ሁለተኛ ጨዋታው ነው ይሄን እያስተካከልን እንሄዳለን።

ራሳችን በሳትናቸው ኳሶች ዋጋ ከፍለናል (ፍስሀ ጥዑመልሳን ድሬዳዋ ከተማ)

ስለ ዛሬው ጨዋታ

በዛሬው ጨዋታ ራሳችን በሳትናቸው ኳሶች ዋጋ ከከፍለናል ። ያለውን ነገር አስተካክለን ለቀጣይ መቅረብ ነው።

በመጀመርያው አጋማሽ ላይ በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ያገኛችሁትን የሰው ቁጥር ብልጫ መጠቀም አልቻላቹም ተደጋጋሚ ደሞ ተከላካይ ክፍላቹ ሲረበሽ ነበርና እዚ ጉዳይ ላይ እንዴት ነው

ቁጥር ብልጫው እንኳን ችግር የለውም ኣንድ ቡድን ስነልቦናውም ይጠነክራል። ዞሮዞሮ ይሄ ሰበብ ሊሆን አይችልም። የአንድ ሰው ቁጥር ብልጫውን መጠቀም ነበረብን። አሁን በዳኛም በምንም ማሳበብ አልችልም መጀመርያ የሳትናቸው ኳሶች ዋጋ አስከፍለውናል 45ደቂቃ ከእረፍት በኃላ ግን ኳስ አልተጫወትንም ተጫዋቾች ሲተኙ ነው የዋሉት። የሚያሳዝነው እኔ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የት እንደሚደርስ ኣላውቅም። ተጫዋች ሲተኛ ነው የዋለው እና በዛው ተጠናቀቀ አጥቅተን ለመጫወት ሞክረናል ግን ሁሉም ጎል ውሰጥ ሰለነበሩ በሁለት ተከላካይ ነው የተጫወትነው ከእረፍት በኃላ አንዳንዴ ነው ሶስት ሲሆኑ የነበሩት።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer