አስተያየት | ወልቂጤ ከተማ 0-2 አዳማ ከተማ

 

አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ – የአዳማ ከተማ ምክትል አሰልጣኝ

ስለጨዋታው

” በጨዋታው ያሰብነውን ያህል ኳሱን ተቆጣጥረን መጫወት አልቻልንም። በውጤት ደረጃ ብናሸንፍም በእንቅስቃሴ ረገድ ጨዋታው ያሰብነውን አይገልጽም። ውጤቱ የእኛን እንቅስቃሴ የሚገልፅ አይደለም ::”

አስበን ወደ ሜዳ የገባነው የነበረው ኳሱን ይዘን መጫወት ነበር። በእረፍት ሰአትም የተነጋገርነው ጨዋታችን ልክ እንደልነበረ ነው ::

ታክቲካሊ ተጫዋቾቻችን ሙሉ ለሙሉ ያሰብነውን አልተገበሩልንም ማለት እንችላለን። ሁላችንም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን ብለን ነበር የገባነው። የጨዋታው ውጤቱ ጥሩ ቢሆንም ጨዋታችን ረጃጅም ኳሶች ይበዙት ነበር።”

ተጫዋቾቼ ሰአት የመግደል ነገር በፍፁም አላሰብነውም ለግብ ጠባቂያችንም ቢሆን እንዲህ አይነት ነገሮች እንዳይደረጉ መልእክቶችን ልከናል ::

አሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛው – ወልቂጤ ከተማ

ጨዋታው ቆንጆ ነበር በቅድሚያ አዳማዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ። ተጫዋቾቻችን እንዳያችሁት በ90 ደቂቃ ውስጥ አቅማቸው የፈቀደውን አድርገዋል።

በእግርኳስ ውስጥ ያልተጠበቀው ነገር ይከሰታል። በእርግጥ በመጀመሪያው 45 ብልጫዎች ተወስደውብን ነበር፤ ከኛ የተሻለ መንቀሳቀስ ችለው ነበር :: በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ክፍተቶቻችን አርመን የተሻለ ነገር ለመስራት ሞክረን ነበር። በዚህም በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ ብንችልም አጋጣሚዎችን መጠቀም አልቻልንም። እንደ ጨዋታ ግን ተጫዋቾቼ ውጤቱን ለመቀልበስ ባደረጉት ተጋድሎ እጅግ ደስተኛ ነኝ።”

የመከላከል አደረጃጀታችን ባለፉት ጨዋታዎች ጠንካራ ነበር በዛሬው ጨዋታ ላይ ግን አራቱም ቋሚ የተከላካይ ክፍል ተጫዋቾቻችን በጉዳት ያጣንበት ሁኔታ ነበር ::

ተጫዋቾቼ ባሳዩት ነገር ደስተኛ የተገኘውን ውጤት በፀጋ ነው የምንቀበለው ያለውን ውጤቱ ሙሉ ሀላፊነትን የምወስደው እኔ ነኝ ለተጫዋቾቼ ከፍ ያለ ምስጋና በዚህ አጋጣሚ የማቀርበው ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor