አስተያየት | ወላይታ ድቻ 1-0 ባህርዳር ከተማ

ጨዋታው በኛ ሜዳም እንደመሆኑ መጠን አጥቅተን ለመጫወት ነው የገባነው (ደለለኝ ደቻሳ የወላይታ ድቻ ጊዚያዊ አሰልጣኝ)

ስለጨዋታው

ጨዋታው በኛ ሜዳም እንደመሆኑ መጠን አጥቅተን ለመጫወት ነው የገባነው። እንዳያችሁት በጣም ከባድ ነበር። ባህርዳር ጥሩ ቡድን ነው። በጣም ጥሩ ጨዋታ ነበር ብየ አስባለው።

ውጤታማ የአጥቂ እና ተከላካይ ለውጥ አድርገሀል እና ምክንያቱ ምንድነው ይህ ያልተለመደ ቅያሪ እንድታደርግ ያረገህ

በአጠቃላይ ስናይ ይህ ጨዋታ ለኛ በጣም ወሳኝ ስለነበር ደጉ ደበበን ከነ ጉዳቱ ነበር ያስገባነው። ባየም እንዳያችሁት ከነ ጉዳቱ ነው ያስገባችሁት። በደጉ ቦታ የሚጫወት ተጫዋይ ስለነበረን ባየን መጠቀ ችለናል።

በቀጣይነት ከወላይታ ድቻ ስለሚኖረው ቆይታ

እውነቱን ለመናገር እኔ አሰልጣኝ ሆኜ ከምቀጥል ይልቅ ቡድኑን ነው ማስቀድመው። ምክንያቱም እኛ የምኖረው ድቻ ሲኖር ነው። የክለቡ መኖር ለኔም ስለሚበጅ የክለቡ አመራሮች የሚያስተላልፉት ማንኛውም ውሳኔ በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።

ያገቡትን ግብ ኣስጠብቀው መውጣት ችለዋል (ፋሲል ተካልኝ ባህርዳር ከተማ)

ስለጨዋታው

እንግዲህ ያው መጀመርያ ተጋጣሚያችን ሶስት ነጥብ ስላገኙ። እንኳን ደስ ኣላቹ ማለት እፈልጋለሁ። ሁለት የተለያየ 45 ደቂቃ ነው የነበረው። በመጀመርያ 45ደቂቃ ከክንፍ የሚመጡ ተሻጋሪ ኳሶችን ተከላክለን የራሳችንን ጨዋታ ለመጫወት ነበር የሞከርነው። ግን እንደምናስበው ኣጥቅተናል ወይም የግብ ዕድል ፈጥረናል ማለት ኣልችልም። በሁለተኛው 45 ይበልጥ ወደነሱ የግብ ክልል በደምብ ተጭነን ጎሎችን ለመፍጠር ሞክረናል ያሰብነውን ያህል የጎል ዕድል ፈጥረናል ባልልም በሁለተኛው 45 የተሻልን ነበርን። ግቦችን ማግባት ኣልቻልንም እነሱም ያገቡትን ግብ ኣስጠብቀው መውጣት ችለዋል።

ከዳኝነት ጋር ተያይዞ በነበረው ተቃውሞ

እናንተም ሁል ጊዜ ስለዳኝነት ትጠይቃላቹ።ብዙ ስለዳኛ ማውራት ኣልፈልግም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ግን የሚበጀው ሜዳው ላይ የታየውን ነገር እናንተ ብትወግቡ የተሻለ ነው። ሁል ግዜ ኣሰልጣኞች ለምንድነው ዳኝነት ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙት ሚለውን ማየት አለባቹህ። ስናሸንፍም ሰንሸነፍም ሜድያ ፊት ቁሜ ዳኞችን ቅሬታ ማቅረብ ኣልወድም ለቡድኔም ይጠቅማል ብየ ኣላስብም።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor