አስተያየት| አዳማ ከተማ 2-0 ወልዋሎ አ.ዩ.

👉👉መደበኛ ልምምዶችን በአግባቡ የሰራንበት ሳምንት ይሄኛው ነበር።” (ደጉ ዱባም አዳማ ከተማ)

👉👉”በዳኛ አካባቢ ያያችሁትን ነገር መናገሩ ትርጉም ያለው አይመስለኝም።” (ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ – ወልዋሎ አ.ዩ.)

 

ም/አሰልጣኝ ደጉ ዱባም – አዳማ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“እንዳያችሁት ጨዋታው ጥሩ ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ ለማጥቃት ነበር የተጫወትነው፤ የነበረው እንቅስቃሴ ጥሩ ነው።”

ስለ ተጋጣሚ ቡድን

“ወልዋሎ ጉዳትም አለበት፤ ተከታታይ ጨዋታ በመሸነፉ በሞራልም ረገድ ትንሽ መውረድ አለ። ከነበረበት ችግር አኳያ ዛሬ የነበረው እንቅስቃሴ መጥፎ አይባልም።”

ስለ አዳማ ተጫዋቾች ጥያቄ

“አሁን ሁሉም ነገር ጥሩ ነው፤ መስመር ይዟል፤ ግንኙነቱ አሁን የተሻለ ነው። መደበኛ ልምምዶችን በአግባቡ የሰራንበት ሳምንት ይሄኛው ነበር።”

ም/አሰልጣኝ ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ – ወልዋሎ አ.ዩ.

 

ስለ ጨዋታው

“ያው ጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የተከላካያችን ጥንቃቄ አለማድረግ ዋጋ አስከፍሎናል። የገባው ጎል ያው በራሳችን ችግር ነው። በመጀመሪያው አጋማሽ 2-1 መሆን እንችል ነበር፤ የኛ ተጫዋቾች ግን ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።”

ስለ ዳኛ

“በዳኛ አካባቢ ያያችሁትን ነገር መናገሩ ትርጉም ያለው አይመስለኝም። እናንተም ስላያችሁት መዘገብ ትችላላችሁ። በመጀመሪያው አጋማሽ ፍፁም ቅጣት ምት ሁለተኛው አጋማሽ የገባው ጎል ለናንተ ነው የምተወው። ሌላ የምለው ነገር የለኝም።”

ስለደጋፊው

“ደጋፊው ለኛ ጥሩ ክብር ነው የሰጠን። ማመስገን ነው የምንፈልገው። ከዛ ውጪ ያለው ግን እናንተ ባለሙያዎች ስለሆናቹ መዘገብ ትችላላችሁ።”

ስለ አቋም መውረድ

“የቋሚ ተሰላፊ የሆኑ 4 ወይም 5 ተጫዋቾች ጉዳት ላይ ነው ያሉት፤ እስካሁንም አልዳኑም።”

ስለ ቀጣይ እቅድ

“በቀጣይ ያሉብንን ችግሮች በሚገባ አስተካክለን ጥሩ ነገር እንሰራለን ብለን እናስባለን።”

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor