አስተያየት| ሲዳማ ቡና 3-2 አዳማ ከተማ

 

የ 13ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬም ሀዋሳ ላይ ሲደረግ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 3-2 ካሸነፈ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ስለ ጨዋታው የሚከተለውን ብለዋል።

ጨዋታው ለአሰልጣኞች ትንሽ አስቸጋሪ ነበር (ዘርዓይ ሙሉ ሲዳማ ቡና)

ስለጨዋታው

ጥሩ ጨዋታ ነበር። በሁለታችንም በኩል ማጥቃት ላይ የተመሰረተ አጨዋወት ነው። ለደጋፊም ማራኪ ነው። ጨዋታው ለአሰልጣኞች ትንሽ አስቸጋሪ ነበር። መከላከል ላይም ችግር ነበር መስተካከል ያለበት ነገር ነው። ምክንያቱም የቆሙ ኳሶች እና የሚሻሙ ኳሶች ያቸው የገቡብን። አዳማ ኳስ የሚጫወት ጥሩ ቡድን ነው። በአጠቃላይ ጥሩ የኳስ ፍሰት የታየበት ጨዋታ ነው ብየ አስባለው።

በቀላሉ ግብ ስለሚያስተናግደው ተከላካይ ስፍራ

እሱን ብያለው ተመሳሳይ ነው። የተቆጠሩብን ግቦች የቆሙ እና የሚሻሙ ናቸው። እኛም ከሷን ተቆጣጥረን በመጫወት ነበር ስናልፍ የነበረው። ተከላካዮቻችን ከተጋጣሚው ጋር ተመሳሳይ ነበር ይቻላል። እኛ ጋር የቆሙ ኳሶችን የመቸገር ሁኔታ አለ። እነሱ ደግሞ ፍጥነት ስለሌላቸው ኳስን በመቆጣጠር ነበር ስናልፍ የነበረው። እኛም ተሳክቶልናል።

ስለ ግቧ መሻር

እሱን ለዳኛው ትቸዋለው። ህዝቡም ያየው ነገር ስለሆነ። ህዝብ ይመልሰው። ዳኛው እራሱ ይፍረደው።

አንድ ዳኛ ዳኛ እስከሆነ ድረስ በእኩል አይን ማጫወት አለበት (አስቻለው ኃ/ሚካኤል የአዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ)

ስለጨዋታው

ጨዋታው እንዳያችሁት ጥሩ ጨዋታ ነበር የተካሄደው በሁለታችን በኩል። ግን አስምሬ መናገር የምፈልገው ባለፈውም ተናግሪያለው ዳኞች ከሜዳ ውጭ ለሚጫወተው ቡድን ተፅእኖ እያሳደሩ ነው። ፌደሬሽኑም እዚ ላይ መስራት አለበት። አንድ ዳኛ ዳኛ እስከሆነ ድረስ በእኩል አይን ማጫወት አለበት። ጥሩ ኢንተርናሽናል ዳኞች አሉ ውጭ ሳይቀር ሄደው የሚያጫውቱ ከነሱ ልምድ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ዋና ዳኛው ጥሩ ነበር ረዳቶቹ ግን ምንም አላገዙትም። ፌደሬሽኑ ያስብበት እውነተኛ ዳኝነት እንፈልጋለን። ሁለታችንም ጥሩ ኳስ ነው የተጫወትነው ያገኘናቸው ኳሶች ባለመጠቀማችን ግን ዋጋ አስከፍለውናል። ተጫዋቾቻችን ስሜታዊ ያደረጉት ዳኞች ናቸው። በመጨረሻ የዳኝነቱ ነገር በደምብ ይታሰብበት።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor