አስተያየት| መቐለ 70 እንደርታ 5-1 ሀዋሳ ከተማ

👉👉 ወሳኝ ነበር ምክንያቱም ባሳለፍነው ጨዋታ ከሽንፈት ነው የመጣነው ዛሬ ግድ ማሸነፍ ነበረብን አሸንፈናል (ጎይትኦም ሀይሌ የመቐለ 70 እንደርታ ምክትል አሰልጣኝ)

👉👉 ተጨዋቻችን በካይ ካርድ መውጣቱ ትንሽ በላይነቱን እንዲወስዱ አድርጓል ግን በሁሉም መልክ እነሱ ጥሩ ነበሩ ሚገባቸውን ውጤት ነው ያስመዘገቡት (አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ሀዋሳ ከተማ)

 

የ 14ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሲጀመር መቐለ 70 እንደርታ ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ 5-1 ከሸነፈ በኋላ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ምክትል አሰልጣኝ ጎይትኦም ሀይሌ መቐለ 70 እንደርታ

“ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር።ለእኛ ጨዋታው ወሳኝ ነበር ምክንያቱም ባሳለፍነው ጨዋታ ከሽንፈት ነው የመጣነው ዛሬ ግድ ማሸነፍ ነበረብን አሸንፈናል።በተጨዋቾቹ ላይ የነበረው መነሳሳት ጥሩ ነበር፤እኛም ይሄን ሳምንት በሚገባ አነሳስተናቸው ነበር ባጠቃላይ ጥረ ጨዋታ ነበር።”

ስለ ዋንጫ ፋክክር

“አሁንም ከመሪዎቹ አልራቅንም የነገ የነሱ ውጤትንም እንጠብቃለን ቀሪ ጨዋታዎች ለኛ ወሳኝ ናቸው።”

አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ሀዋሳ ከተማ

“ጨዋታው ከጠበቅነው በላይ ነው።ይሄን አልነበረም የጠበቅነው የመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ልንቆጣጠር ነበር ሀሳባችን ግን አልሆነም።በ10 ደቂቃ አካባቢ ውስጥ ሁለት ግቦች አግብተውብናል እናም ያነገር አነሳስቶዋቸዋል።በዛ ላይ ደግሞ ተጨዋቻችን በካይ ካርድ መውጣቱ ትንሽ በላይነቱን እንዲወስዱ አድርጓል ግን በሁሉም መልክ እነሱ ጥሩ ነበሩ ሚገባቸውን ውጤት ነው ያስመዘገቡት።”

ስለ ቀይ ካርዱ

“የዳኛ ውሳኔ ነው።ተጨዋች ውስጥ ምን እንደሚል አይታወቅም ዳኛው ቅርብ ነው ግን ሊታገሰው ሚገባ ይመስለኛል ምክንያቱም ሁለት ግብ ገብቶብናል በቀይ ካርድ በወጣበት ሰዐት ላይ በጣም መቐለ እያጠቃን ትንሽ ቢታገስ ጥሩ ነበር።የመጀመርያው ጥፋት ለመሸፈን ነበር ሲሞክር ቢጫ ያየው ልጁን መታገስ ነበረበት ያርገውን አላውቅም በፍጥነት ነው በቀይ የወጣው፣የእሱ መውጣት ጎድቶናል።”

ከሜዳቸው ውጪ ስላለው ውጤት

“ይሄንን ምናያይዘው ከሜዳው ጋር ነው።ስንወጣ ሜድው አስቸጋሪ ነው እኛ ምንሰራበት ሜዳ እና ውጪ ላይ ያለው ሜዳ አንድ ዓይነት አይደለም ከዛ አንፃር ነው ምናየው።”

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer