አስተያየት| ሀድያ ሆሳዕና 0-1 ወላይታ ድቻ

👉👉 አቅደን የመጣነው ነገር አሳክተናል (ደለለኝ ደቻሳ የወላይታ ድቻ ጊዚያዊ አሰልጣኝ)

👉👉እድል ከኛ ጋር አልነበረችም እንጂ በሁለተኛ አጋማሽ በርካታ አጋጣሚዎችን ፈጥረናል (ፀጋዩ ኪዳነማርያም የሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ )

 

ቀሪ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ሀዋሳ ላይ በተጣለበት ቅጣት ምክንያት ወላይታ ድቻን ያስተናገደው ሀድያ ሆሳዕና በወላይታ ድቻ 1-0 አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞቹ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

አቅደን የመጣነው ነገር አሳክተናል (ደለለኝ ደቻሳ የወላይታ ድቻ ጊዚያዊ አሰልጣኝ)

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው እንዳያችሁት በጣም ከባድ ጨዋታ ነው። ሀድያ ሆሳዕና በስብስብ ስናየው በጣም ጥሩ ቡድን ነው በዛ ልክም ነው እኛ ተዘጋጅተን ነው የመጣነው። አቅደን የመጣነው ነገር አሳክተናል”።

በሁለተኛው ግማሽ መቀዛቀዛቸው

“ሀድያ ጥሩ ቡድን ነው። የኛ ተጫዋቾች ወጣቶች ናቸው። ሆኖም ግን እንደ ወላይታ ድቻ በመጀመሪያው አጋማሽ እና በሁለተኛው አጋማሽ ነጥብ ለመያዝ እየሰራን ስለሆነ አጨዋወታችን ይለያያል። በመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ከማግባታችን በፊት እና ካገባን በኋላ ጥሩ ነበርን። ሁለተኛው አጋማሽ ግን የኋላ መስመራችንን ደፍነን በህብረት ለመጫወት ነው ሙከራ ያደረግነው”።

እድል ከኛ ጋር አልነበረችም እንጂ በሁለተኛ አጋማሽ በርካታ አጋጣሚዎችን ፈጥረናል (ፀጋዩ ኪዳነማርያም ሀድያ ሆሳዕና)

ስለጨዋታው

በጣም ጥቂት ቀናቶች ናቸው ከቡድኑ ጋር ቆይታ ያደረኩት። አራት ግዜ ብቻ ነው ልምምድ ያሰራሁት። ዛሬ ደግሞ ቡድናችን በውድድር ምን መልክ እንዳለው ለማየት ችያለው። በነበረው እንቅስቃሴ የመጀመሪያዎቹ ሀያ ደቂቃ የድቻ የበላይነት ነበር ማለት ይቻላል። በቀሩት ደቂቃዎች እና በሁለተኛው አጋማሽ በሙሉ ተጭነን መጫወት ችለናል። እድል ከኛ ጋር አልነበረችም እንጂ በሁለተኛ አጋማሽ በርካታ አጋጣሚዎችን ፈጥረናል። እንደ እንቅስቃሴ ድቻ በጥሩ መነቃቃት ያለ ቡድን ነው። እኛ ደግሞ ከሜዳችን ውጭም እንደመጫወታችን መጠን ጫናዎች አሉብን ተጫዋቾቼም ጫና ውስጥ ናቸው። የነጥቡም መራራቅ ተጨማሪ ጫና እንዳያሳድርብን እየሰራን ነው ያለነው። ይህ የመጀመሪያ ጨዋታየ ነው ብዙ ነገሮችን አሳይቶኛል። ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አሉ ከነዚህ ስህተቶቻችን መነሻነት አድርገን እንሰራለን። በአብዛኛው ሁለተኛው ዙር ላይ አሻሽለን እንቀጥላለን።

ያገኙትን አጋጣሚ ወደ ግብ የመቀየር ችግር

ወደ ግብ ደርሰናል። የአጨራረስ ችግር ግን ነበረብን። እሱን ለማስተካከል ግዜ ይፈልጋል በቀጣይ እንፈታዋለን።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor