አስተያየት| ሀዋሳ ከተማ 3-2 ፋሲል ከተማ

👉👉የመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ትንሽ ተዘናግተን ነበር ቢሆንም ተረጋግተን ምላሽ ሰጥተናል አምጣቸው ኃይሌ ረዳት አሰልጣኝ (ሀዋሳ ከተማ)

👉👉ሁለት ግብ ማስቆጠራችን ቡድኑ ውስጥ የፈጠረው መላላት ለተጋጣሚ ቡድን ጥንካሬ ሰጥቷቸዋል (ስዩም ከበደ ፋሲል ከተማ)

አስተያየት| ሀዋሳ ከተማ 3-2 ፋሲል ከተማ

አዝናኝ የነበረው የ15ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀዋሳ ላይ ሀይቆች ፋሲል ከተማን አስተናግደው 3-2 ካሸነፈ በኋላ። አሰልጣኞች ሀሳባቸውን ሰጥተውናል።

የመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ትንሽ ተዘናግተን ነበር ቢሆንም ተረጋግተን ምላሽ ሰጥተናል አምጣቸው ኃይሌ ረዳት አሰልጣኝ (ሀዋሳ ከተማ)

ስለጨዋታው

ጨዋታው እንደጠበቅነው ነው የሄደው። እኛም ይህን ጠብቀን ነበር። የመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ትንሽ ተዘናግተን ነበር። ቢሆንም እኛም ተረጋግተን ምላሽ ሰጥተናል። ግብ ተቆጥሮብናል የተቆጠረውን ግብ ሳያስቡ ተረጋግተው እንዲጫወቱ ነው ለተጫዋቾቻችን የነገርነው። በተለይም ከኋላ መስመር የነበረው ጥሩ አለመሆን ግብ እንዲቆጠርብን አርጓል።

ሁለት ግብ ማስቆጠራችን ቡድኑ ውስጥ የፈጠረው መላላት ለተጋጣሚ ቡድን ጥንካሬ ሰጥቷቸዋል (ስዩም ከበደ ፋሲል ከተማ)

ስለጨዋታው

በአጠቃላይ የመጀመሪያ ሀያ እና ሀያ አምስት ደቂቃዎች ጨዋታውን ተቆጣጥረን መጫወት ችለናል። ኳስ በመቆጣጠር ረገድ እና ወደ ፊት በመሄድ ላይ የተሻልን ነበርን። በዚህም ሁለት ግቦችን አስቆጥረን ከዚህ በተሻለ ብዙ ምንራመድ ይመስል ነበር። ሁለት ግብ ማስቆጠራችን ቡድኑ ውስጥ የፈጠረው መላላት ለተጋጣሚ ቡድን ጥንካሬ ሰጥቷቸዋል። ምክንያቱም የተቆጠሩብንን ግቦች ስንመለከት በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ትኩረት ማድረግ ስንችል እንደቀልድ ተቆጥረውብን ዋጋ አስከፍለውናል። ሀዋሳዎች ተስፋ ባለመቁረጥ ያደረጉት ተጋድሎ ምሳሌ የሚሆን ነው። በአጠቃላይ በራሳችን የሰራናቸው ስህተቶች ዋጋ አስከፍለውናል።

የተከላካይ ስህተት

ተከላካይ መስመሬ ብዙም ደካማ አደለም ነገር ግን ዛሬ ቡድኑ ዘግቶ ከመሄድ ጋር የሚገባውን ነገርጠማድረግ አልቻለም ይህም ሚስተካከል ነገር ነው።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor