አስተያየት| ሀዋሳ ከተማ 1-0 ጅማ አባ ጅፋር

 

የ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬም ሲቀጥል ሀዋ ሳላይ ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ 1-0 ካሸነፈ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።

የኋላ መስመራችንን በጥንቃቄ ነበር ሲጫወት የነበረው (አዲሴ ካሳ ሀዋሳ ከተማ)

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነው ያው ጎል ለማግባት የሚደረግ ጥረት ላይ እንዲ አይነት ነገር ይፈጠራል። እነሱም አጋጣሚዎች አግንተዋል በመልሶ ማጥቃት ነበር የተጫወቱት ካለለፈው ጨዋታ የሆነ ነገር ወስደናል። የኋላ መስመራችንን በጥንቃቄ ነበር ሲጫወት የነበረው። ትንሽ ክፍተት ቢኖር የሆነ ችግር ይፈጠር ነበር። ግን ጨዋታው ከባድ ነበር በተለይ ለእንደኛ አይነት ቡድን። የአጥቂው መስመር ላይ ያለው ሄኖክ አየለ ነው ሄኖክ አሁን መጫወትን ነው ሚያሰበው። በፊት ኳሶችን ጠብቆ ይጨርሰ ነበር አሁን ግን ከዛ ወጥቷል። የሚሻሙ ኳሶች በጣም ዋጋ እያስከፈሉን ነበር። እየተጠቀምን አልነበረም ለነሱ ደሞ እንዲህ አይነት አጨዋወት አመቺ ነበር ሄኖክ አስጨንቆ ሊጫውት አልቻለም ነበር አና ሁለትኛ አጋማሽ ላይ ተሳክቶልናል።

በጊዜ ነበር የሜዳ ላይ የተጫዋች ብልጫ የነበራቹ ግን ስትጠቀምበት አልታየም

ብልጫ አልነበረም ማለት አይቻልም ብልጫ እማ ነበርን። ጨዋታው በሙሉ በተለይ ተጨዋቹ ከወጣ በኋላ ጨዋታው መልሶ ማጥቃት ነበር። በግራም በቀኝም ብታይ ሁሉንም ኳስ ብታይ የቁጥር ብልጫ ሳይሆን እነሱ በጣም ይከላከላሉ ቦታውን አይለቁትም ነበር። ያን ቦታ ከለቀቁት ደግሞ የቁጥር ብልጫው ምንም ትርጉም አይሰጥም ሁለቱንም 45 ደቂቃዎች እነሱ ሜዳ ላይ ነበር ጨዋታው ቆመክ ምትጫወት ከሆነ በጣም ከባድ ነገር ነው።

እኔ ስለ ዳኛ ምንም ማለት አልፈልግም ማውራት ምፈልገው ስለ እራሴ እና ስለቡድኔ ነው (ጳውሎስ ጌታቸው ጅማ አባ ጅፋር)

ስለ ጨዋታው

መጀመሪያ ሀዋሳዎችን እንኳን ድስ ያላቹህ ለማለት እወዳለው። በመቀጠል ጨዋታው እንዳያችሁት ሳቢ ነበር። እዚያም እዛም ሲሞከር ነበር ብዙ ነገር አይታችኋል። የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ቀይ ካርድም ነበር ጨዋታውን በሙሉ በጎዶሎ ተጨዋቾች ነው የጨረስነው በመልሶ ማጥቃት ነበር የተጫውትነው። እኔ ስለ ዳኛ ምንም ማለት አልፈልግም ማውራት ምፈልገው ስለ እራሴ እና ስለቡድኔ ነው። ሙሉ 90ደቂቃ የሚችሉትን ሁሉ አርገዋል የመጨረሻውንም ሰዓት እንደዚህ ነው ምለው ነገር የለም። ፍርዱን ለእናንተው ትቻለሁ ባጠቃላይ ግን የጨዋታው እንቅስቃሴ ለኔ ጥሩ ነበር። ግን ያው ጨዋታ እንዳያምር የሚያደርጉትም ዳኞች ናቸው እንዲያምር ሚያደርጉትም ዳኞች ናቸው ባጠቃላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ነበር።

ስለ ተጨዋቾች ስሜታዊ መሆን

እናንተ የተመለከታቹት የተጨዋቾችን ሰተት ነው ተጨዋቾቹ ገና ወጣቶች ናቸው ቶሎ ስሜታዊ ይሆናሉ። መጀመሪያ እናንተ መቅረፍ ያለባቹ ሜዳ ላይ ያለውን ሰተት ነው የሜዳው ስተት ከተቀረፈ ሁሉም ነገር በትክክል የተጫወት ያሸንፍ። ለኢትዮጵያ ኳስ እድገትም ሚበጀው እንዲህ ቢሆን ነው።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor