አስራት መገርሳ ማረፍያ ታውቋል

 

ቁመተ መለሎው አማካዩ አስራት መገርሳ ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል።

ይህ አንጋፋ የቀድሞ የደደቢት፣ዳሽን ቢራ፣ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አማካይ በሁለተኛው ዙር እራሳቸውን ጠንካራ አድርገው በሁለተኛው ዙር ለመቅረብ እየጣሩ ያሉት ስሑላውያኑን በአንድ አመት የኮንትራት ውል ነው መቀላቀል የቻለው። በመጀመሪያው ዙር ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩት ስሑላውያኑ በአዲስ አሰልጣኛቸው ሲሳን አብርሀም እየተመሩ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመዝለቅ በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም ዮናታን ከበደ እና ራሂም ኦስማን ማስፈረማቸው ይታወሳል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor