አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ የመጀመሪያው አሰልጣኝ? ወይስ?ኮሮናን ለማጥፋት 30 ሺብር ለግሷል

🔑 አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ
የመጀመሪያው አሰልጣኝ? ወይስ?ኮሮናን ለማጥፋት 30 ሺብር ለግሷል

🔑 የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን
500ሺ ብር ለግሷል

🔑ፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ ሽፈራውም
400 አቅመ ደካሞችን እያገዘ ነው…


የወልዋሎው አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያደረገ ላለው የኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚውል 30ሺ ብር አበርክቷል፡፡

የስፖርት ቤተሠቡ ቫይረሱን የመከላከል ስራውን በሚችለው መጠን እያገዘ ሲሆን በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ500 ሺብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ፌዴሬሽኑ ከህብረተሰቡ የሚገኘውን በተለይ በሲቲ ካፑ ገቢ የሚያገኘው ገንዘብ ሲጠቀምበት መቆየቱን አውስቶ አሁን ደግሞ ይህን ቫይረስ ለመከላከል ከህዝቡ የሚያገኘውን መልሶ ለህዝቡ ለመስጠት በመቻሉና የችግር ጊዜ አጋርነቱን በማረጋገጡ መደሰቱን ገልጿል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ማህበርም ከሰሞኑ ወደ 500ሺብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡

ፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ ሽፈራውም ለ400 አቅመ ደካሞች የማክስ ሳሙናና ጓንት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ /የሌሎች ርዳታ መስጠት ካልተደበቀ በስተቀር / ከአሠልጣኞች መሃል አሰልጣኝ ዘማርያም የመጀመርያ የሚያደርገውን ድጋፍ አድርጓል፡፡ ሌሎች አሰልጣኞችም የሙያ ጓደኛቸውን አርአያነት ይከተላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የየክለቦች ተጨዋቾችም የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ በማድረግ የችግር ወቅት ደራሽነታቸውን ያረጋግጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡”የአለም ችግር የሆነው ኮሮና ከሃገሬ ብሎም ከመላው አለም ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ላይ የበኩሌን በማድረጌ ደስ ብሎኛል ብሏል.. አሰልጣኝ ዘማርያም….የኢትዮጲያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበርም የ50ሺ ብር ድጋፋቸውን ለጤና ሚኒስቴር አስረክበዋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport