መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከክለባቸው ሊለያዩ ነው
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከክለባቸው ሊለያዩ ነው

አጋራ
አጋራ

 

 የጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ  አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከክለቡ ጋር ለመለያየት መቃረባቸውን ገለጹ፡፡

አሰልጣኙ ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ እንደገለፁት “ለክለቡ ያስገባሁት የመልቀቂያ ደብዳቤ በአመራሮቹ ተቀባይነት አግኝቷል “

“ከክለቡ ጋር ለመለያየት የወሰንኑኩት ለቤተሰቦቼ በቂ ጊዜ ለመስጠት በማሰብ ነው፤  ክለቡን ማሰልጠን ከጀመረኩበት ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ የተሳካ ስራ መስራት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል፡፡

የጅማ ከተማ እግር ኳስ  ክለብን ማሰልጠን መነሻ ባደረጉበት  የመጀመሪያ ዓመት የከፍተኛ ሊግ ውድድሩን አራተኛ ሆኖ እንደጨረሰ  አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት ከ ምድብ “ለ” አንደኛ ሆኖ በመምራት ላይ እንደሚገኝም  ገልጸዋል፡፡

የክለቡ ፍላጎት በ2010ዓም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ መሆኑን የገለጹት አሰልጣኙ “ከቤተሰብ ተለይቼ የክለቡን ፍላጎት ለማሳከት እንደማልችል በመገንዘቤ ለመልቀቅ ወሰኛለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“በማሰልጠን ቆይታዬ የክለቡ ደጋፊዎች የጅማ ከተማ ነዋሪዎችና ተጫዋቾች ከጎኔ በመሆን ያበረታቱኝ በመሆኑ ምስጋናዬ ከፍተኛ ነው” ብለው፡፡

ስለሁኔታው የተጠየቁት የክለቡ አመራሮች መረጃ የሚሰጡት ጉዳዩ ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ገልጸዋል።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...