አሰልጣኝ ከማል አህመድ አደም ሊያሳትሙት አስበው ስለነበር መፅሀፍ እና ስለ አካዳሚያቸው ይናገራሉ።

👉👉እኛ ውድድር ወደ ምንወዳደርበትን መንገድ ካልገባን ማንም መጥቶ ከከማል አካዳሚ ታዳጊዎች ፈልገናል እና እንውሰድ ብሎ የሚል የለም

👉👉ይህን መፅሀፍ አሳትሜ ለወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል የሚል ሀሳብ ነበር የነበረኝ

 

በስኬት ደረጃ እና ሀገሪቱን የሚጠቅሙ ተጫዋቾች ለይተው ሲያወጡ የንስር አይን ናቸው። ሀዋሳ ከተማን ይዘው 1996,1999 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፍ አድርገው በማንሳት ለብዙ አመታት ያክል ጅማ አባ ጅፋር ዋንጫ እስካነሳበት ድረስ ሀዋሳ ከተማን ብቸኛው የሊጉን ዋንጫ ያነሳ የክልል ክለብ አሰኝተውታል። ከዛ በተጨማሪም በ1997 የኢትዮጵያ ዋንጫ በማሸነፍ ሀዋሳን እየመሩ በኮንፌደሬሽን ዋንጫ በአፍሪካ መድረክ መሳተፍ የቻሉ አንጋፋ አሰልጣኝ ናቸው የዛሬው እንግዳችን አሰልጣኝ ከማል አህመድ። ኢትዮጵያ ከ31 አመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ብቅ እንድትል ያደረጓትም በብዛት እርሳቸው ያፈሯቸው ተጫዋቾች ናቸው። በእርሳቸው ሂወት ላይ ያነጣጠረ መፅሀፍ ለማፃፍ አስበው የተስተጓጎሉበት ምክንያት እና ስለ አካዳሚያቸው የሚከተለውን ብለዋል።

መፅሀፍ የማሳታም እቅድ ነበራቸው እንዳልተሳካላቸው ነው ያለኝ መረጃ እና ምንድነው ምክንያቱ መፅሀፉ እንዳይታተም መሰናክል እየሆነ ያለበት ምክንያት?

መፅሀፉ የተስተጓጎለበት ምክንያት ያዘጋጁልኛል ብየ ያልኳቸው ሰዎች ያለመመቻቸት ነው። ደግሞም አንዳን እንረዳሀለን ያሉኝም ነበሩ በነበረው የሙስና ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ለማሳተም የሚያስችለኝን የገንዘብ እርዳታ ማግኘት አልቻልኩም። ምክንያቱም መፅሀፉን ለማሳተም 100,000 ብር ነው ስለሚያስፈልገው በዚህ ጉዳይ ሳይሳካ ቀርቷል። ነገር ግን አሁንም አሜን ጠቅላላ ሆስፒታል 15,000 ብር ሰጥቶኝ ነበር። ወራቤ ላይ የሚገኝ አንድ ኮሌጅ ደግሞ 10,000 እነዚህን ብሮች መፅሀፉን ለማፃፍ እና ለአንዳንድ ወጪዎች ተጠቅሚያለው። ያንን ለማስተካከል ሌላ ስፖንሰር የለም። ስፖንሰር እና የሚረዳኝ ሰው ባለመኖሩ ተስተጓግሎብኛል።

መፅሀፉ በምን ላይ ያነጣጠረ ነው በዋነኝነት

መፅሀፉ በኔ ሂወት ነው ያነጣጠረው። አሰልጣኝ ከማል አህመድ ከልጅነት ጀምር ከየት ተነስቶ የት ደረሰ የሚለውን ነገር በሂወቴ ያሳለፍኳቸውን ውጣ ውረዶች። እንዲሁም በስፖርቱ የነበረኝ ነገር ምንድነው የሚለው ነገር ነው የሚያስሰው። ይህን መፅሀፍ አሳትሜ ለወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል የሚል ሀሳብ ነበር የነበረኝ። በተጨማሪም በሀገሪቱ ያለው እግር ኳስ ምን ደረጃ ላይ ነው ሚገኘው። እግር ኳሳችንስ እንዳያድግ እንቅፋት የሆነበት ምክንያት ምንድነው እሚሉት ነገሮችም ተካተውበታል። እናም ሁሉም ነገር ተፅፏል ኤዲት ብቻ ነው የቀረው።

መፅሀፉ እንዲጠናቀቅ ምን መደረግ አለበት

እኔ የምለው አቅሙ ያለው መፅሀፉ እንዲታተም ሁሉም የሚችለውን ቢያደርግ ብሎም እንዲረዱኝ እፈልጋለው። አልያም ደግሞ መፅሀፉ ታትሞ የሚወጣበት መንገድ ቢያመቻቹልኝ። ካልሆነ መፅሀፉ በኔ አቅም የሚታተም አይደለም።

በክለብ ደረጃ አሰልጣኝነት ካቆሙ በኋላስለ አካዳሚው ከፍተው ታዳጊዎችን እያፈሩ ነው ሚገኙት አካዳሚው በምን ደረጃ ላይ ነው

አካዳሚው እውነት ለመናገር እንደኔ ሚከታተለው የለም። አብሮኝ የሚሰራው መለሰ ከበደ ነው ያለው። ሴቶችንም እያፈራን ነው ያለነው። እንደዚም አድርገህ የሚቀበልህ ክለብ ቢኖር ጥሩ ነው። ሶስት ተጫዋቾች ናቸው ከዚህ አካዳሚ ወደ ክለብ ያመሩት ሁለቱ እዚህ የሚገኙት ክለቦች ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ሲወስዷቸው። አንድ ተጫዋች ደግሞ ጊዮርጊስ ወስዶታል። ይሁን እንጂ በስርዓት የበቁ ተጫዋቾችን ለመውሰድ ፍላጎት ያለው ሰው የለም። እና ከዚህ ቀደም ከቡና ጋር ተነጋግረን ነበር። ውል ተዋውለን እዚህ አካዳሚ የሚዘጋጁ ልጆችን ወደ ክለቡ ወስዶ ለመጠቀም ከስንታየሁ በቀለ ጋር ተስማምተን ነበር። ሆኖም ባልታወቀ ምክንያት ግንኙነቱ ተቋርጧል። እዚህ አካዳሚ ውስጥ የሚሰለጥኑ በቤተሰብ ኮሚቴ አቋቁመናል ኮሚቴው ውድድር ውስጥ እንደንገባ የሚያስችለን መንገድ ለመፍጠር አስቦ የተቋቋመ ነው። እኛ ውድድር ወደ ምንወዳደርበትን መንገድ ካልገባን ማንም መጥቶ ከከማል አካዳሚ ታዳጊዎች ፈልገናል እና እንውሰድ ብሎ የሚል የለም። ወደ ውድድር ለመግባት አዳጋች ያደረገብን አንዱ ምክንያት ኤም አር አይ(MRI) ነው።ምክንያቱም ለምርመራ ለአንድ ልጅ ከ6000-7000 ብር ነው የሚጠየቀው እና አካዳሚው ይህን ለማድረግ አይችልም። እኛን የመርዳት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው እና እየረዱን የሚገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና አቶ ገልገሎ ሲሆኑ በተጨማሪም ኤስ ኦ ኤስ ትምህርት ቤት ናቸው። ሌላው ግን ዘወር ብሎ ማየት አይፈልግም። ከ200 በላይ ታዳጊዎች ይዘን የሚያያቸው ሰው ያስፈልጋል። ሁሉም አካላት ሊረዱን የሚችሉበት መንገድ መማቻቸት አለባቸው።

የውጭ ተጫዋቾች በማምጣት የተለከፉት የፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች አካዳሚውን በቅርበት የሚከታተሉ ይኖራሉ?

እስካሁን አንድም አሰልጣኝ የለም። እዚ እንኳን ያሉት አሰልጣኞች መጥተው የከማል አካዳሚ ታዳጊዎች ለማየት ይቅር እና እዚህ ሰፈር ደርሰው አያውቁም።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor