አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም ድጋፍ አድርገዋል

 

የስሑል ሽረ ዋና አሰልጣኝ በግላቸው በአዳማ ከተማ ድጋፍ አድርገዋል።

 

በአሁኑ ሰዓት አለምን እያስጨነቀ ያለውን የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ለመከላከል የተየያዩ የስፖርት ቤተሰቦች ለቅድመ መከላከል የሚውሉ በተለያየ መንገድ እገዛ እያደደረጉ ይገኛሉ። በዚህም የስሑል ሽረው ዋና አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀም በትውልድ አካቢያቸው አዳማ ከተማ 15 ቀበሌ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የተለያዩ የምግብ አይነቶችን እገዛ አድርገዋል ።ካበረከቱት ቁሳቁሶችም መመካከል እሩዝ፣ ዘይት እና መኮረኒ የመሳሰሉት ይገኙበታል።