አለልኝ አዘነ ቅጣት ተላለፈበት

 

የሀዋሳ ከተማው አማካይ አለልኝ አዘነ ዳኛን በቴስታ ለመምታት በማቃጣቱ በፌደሬሽኑ ተቀጥቷል።

በ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ትግራይ አቅንቶ መቐለ 70 እንደርታን ገጥሞ 5-1 መሸነፉ ይታወሳል። በዚህ ጨዋታ ተጨዋቹ ቢጫ ካርድ የሰጡትን ኢንተርናሽናል አርቢትር ብሩክ የማነብርሃንን በቴስታ ለመማታት ሲያቃጣው በቀይ ተሰናብቶ። የጨዋታ ታዛቢ ኮሚሽነር ያቀረቡትን ሪፖርት ተመልክቶ የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ። ተጫዋቹን ለአንድ አመት ከማንኛውም እግርኳሳዊ እንቅስቃሴ ያገደው ሲሆን 30ሺ ብር እንዲከፍልም ተወስኖበታል። ክፍያው በ7 ቀን ውስጥ ማስገባት አለበትም ተብሏል፡፡

ከአርባምንጭ ወደ ሀዋሳ ከተቀላቀለ በኋላ ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ የወደፊቱ የሀገሪቱ ተስፋ የሚሆን ይህ ተጫዋች በእግር ኳስ እድገቱ ላይ መሰናክል ይሆንበታል ተብሎ ይጠበቃል። ተጫዋቹ የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቱም ተሰምቷል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport