መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ አሁንም እንደ በፊቱ ቀጠሮ ላይ ቀልድ አናውቅም ከተባሉ ያለጥርጥር አባባሉ የሃትሪክ ነው….
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

አሁንም እንደ በፊቱ ቀጠሮ ላይ ቀልድ አናውቅም ከተባሉ ያለጥርጥር አባባሉ የሃትሪክ ነው….

አጋራ
አጋራ

አሁንም እንደ በፊቱ ቀጠሮ ላይ ቀልድ አናውቅም ከተባሉ ያለጥርጥር አባባሉ የሃትሪክ ነው….

እንዳልነው ነገ ጠዋት በቀጠሮው ሰአት እንገኛለን…..በመረጃዎቻችን ዘና ለማለትም ሆነ ቁም ነገር ለመቅሰም ምርጫዎ ያድርጉን አናሳፍሮትም..

*… በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለፉት 15 አመታት ሁለቴ ሃትሪክ የሰራ ያውም በሳምንታት ልዩነት ከፈለጉ እንዳው ልፉ ቢሎት ነው… ብቸኛው ገድለኛ አቡበከር ናስር ግን አድርጎታል…..ሀትሪከኛው ቡናማ ከሀትሪክ ጋር በነበረው ቆይታ የሀትሪኩ መታሰቢያነት ለእናትና አባቴ ይሁንልኝ ብሏል…..

*…የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለክለቦች ደራሽነቱን እያሳየ ነው…ደመወዝ የሚከፍለው አጥቶ በፊፋ ሊታገድ ለነበረው ጅማ አባጅፋር 1.2 ሚሊዮን ብር በማበደር ከጉድ ታድጎታል……

*… የመሃል ሜዳው ኮከብ ጋቶች ፓኖም በ2ኛ ዙር ፕሪሚየር ሊግ በክለብ ታቅፎ እንደሚመጣ ያምናል ከተወሰኑ ክለቦችም ጋር እያወራበት ይገኛል…. ምርጥ ብቃቴን አሳይቼ ብሄራዊ ቡድኑን እንደምቀላቀል ርግጠኛ ነኝም ይላል….

*…እስቲ እንጠይቆት…? የ17ና 20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኖች ምክትል እና የበረኛ አሰልጣኞች በደመወዝ ሳይሆን በቀን አበል እንደሰሩ ያውቁ ይሆን?

*… የሀዲያ ሆሳዕናው አማኑኤል ጎበና ዋንጫ ለመውሰድ ሊጉን መምራት ሳይሆን ዋናው ጠንክሮ አመቱን ሁሉ መፋለም ነው እያለ ነው…..

*…በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ የ5ነጥብ መሪነቱን ያስጠበቀበትን ውጤት በማስመዝገብ የጅማ ከተማ ቆይታውን በውጤት አጠናቋል።

ከውጪ ደግሞ፦

*…ስለ ሪከርድ ሰባሪው ኮከብ ማርከስ ራሽፎርድ ምርጥ ዘገባ ተዘጋጅቶሎታል

*…ህልሙን ዕውን ስላደረገው አዲሱ የሊቨርፑል ፈራሚ ኦዛን ካባክ የምንሎት አለ….

*…በዎልቭስ ስለተረቱበትና አሳዛኝ ነው ስላለው ጉዳይ የአርሰናሉ አለቃ ማይክል አርቴታም ይናገራል….

ነገ ጠዋት ሀትሪክ እጅዎ ስትገባ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያገኛሉ

ነገ ጠዋት ሀትሪክን በእጅዎ ቢያስገቡ ይጠቀማሉ ይዝናናሉ

……ቅዳሜና እሁድዎ የተባረከ ይሁን…….

HatricSport

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...