መነሻ ገጽ ትግራይ ዋንጫ ትግራይ ዋንጫ| ሰሎዳ ዓድዋ ና ስሑል ሽረ አቻ ተለያይተዋል
ትግራይ ዋንጫዜናዎችየትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ትግራይ ዋንጫ| ሰሎዳ ዓድዋ ና ስሑል ሽረ አቻ ተለያይተዋል

አጋራ
አጋራ

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው ትግራይ ዋንጫ የምድብ ሁለት መክፈቻ ጨዋታ የሆነውን የስሁል ሽረ ሰሎዳ ዓድዋ ጨዋታን አስተናግዶ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።

ብዙ ሙከራዎች ባልታዩበት የመጀመርያ አጋማሽ ሰሎዳ ዓድዋ በአንጻሩ የተሻለ መንቀሳቀስ ቢችሉም ብዙ የግብ እድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።ስሁል ሽረ በወገናቸው መስመር ላይ ትኩረት አድርገው ከሁለቱም መስመር በሚነሱ ኳሶች እድሎችን ቢፈጥሩም የእለቱ ኮከብ የነበረው ሰንደይ ሮቲሚ አድኖባቸዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመርያ አጋማሽ በተሻለ መልኩ ጠንካራ ፋክክር ታይቶበታል።በተለይ ስሑል ሽረ የተሻለ በመንቀሳቀስ ከቀኝ መስመር ተቀይሮ በገባው ዓወት ገብረሚካኤል እና ሳሊፍ ፎፎና አማካኝነት ያደረጉዋቸው ሙከራዎች የግቡ አግዳሚ ሲመልሳቸው አብዱልለጢፍ እና ሀብታሙ ያደረጉዋቸው ሙከራዎች ሰንደይ በሚገርም ሁኔታ አድኖባቸዋል።በዚህም የምድብ ሁለት መክፈቻ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።

የህዳር 2 ጨዋታዎች

7:30 | ወላይታ_ድቻ (ከ) ደደቢት
9:30 | መቐለ_70_እንደርታ ከ አክሱም ከተማ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...