መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ “ትውልደ ኢትዮጵያዊን ወደዚህ መጥተው ሀገራቸውን ቢያገለግሉ ለእኛ እጅግ ትልቅ ጥቅም አለው” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

“ትውልደ ኢትዮጵያዊን ወደዚህ መጥተው ሀገራቸውን ቢያገለግሉ ለእኛ እጅግ ትልቅ ጥቅም አለው” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

አጋራ
አጋራ

ከዛሬው ጨዋታ በኋላ የዋልያዎቹ አለቃ ምን አሉ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን በደርሶ መልስ ውጤት 4ለ0 በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸው ተረጋግጧል። ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም የመልሱን መርሀግብር ዋልያው አድርጎ 1ለ0 ካሸነፈ በኋላ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለጋዜጠኞች ሀሳባቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኙ በንግግራቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ መዘጋጀታቸውን ገልፀው በተለይ ተጫዋቾቹ አዕምሯቸው ላይ ከሜዳ ስራ ባለፈ ሳይኮሎጂ ላይ ትኩረት አድርገው መስራታቸው ውጤቱን ለመያዝ በዋናነት እንደረዳቸው የገለፁ ሲሆን በተለይ በሜዳቸው ደጋፊው በተገኘበት ጨዋታን ማድረግ አቅሙ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ጠቁመው በቀጣይ ግን የምድብ ድልድል ጨዋታ ላይ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተን የሰጡት ሀሳብ ትኩረት ስቧል።

“ትውልደ ኢትዮጵያዊን ተጫዋቾች ባላቸው አቅም ተመውዝነው ወደዚህ መጥተው ሀገራቸውን ቢያገለግሉ ለእኛ እጅግ ትልቅ ጥቅም አለው ፣ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የበኩላቸው መወጣት አለባቸው” ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከዛሬው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የተናገሩት ሀሳብ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...