ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የግማሽ ሚልየን ብር ድጋፍ አደረገ

በሀገራችን የህዝባዊ ሩጫ ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ አለም ላይ ለተከሰተውና አለምን እያስጨነቀ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ለመከላከል በሀገራችን እንዳይስፋፋ ለሚደረገው ቅድመ ዝግጅት የሚውል ግማሽ ሚሊየን ብር (500,000.00 ብር) ድጋፍ በሀገራችን ይህን በማስተባበር ላይ ላለው የኮቪድ – 19 ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት አስረክብዋል፡፡

በተጨማሪም በአትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ሁለት ድርጅቶች ፤ ማራቶን ሞተርስ ኢንጅነሪንግ እና ሃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ስም ይህ ወረሽኝ ለመከላከል ለሚደረገው ስራ ድጋፍ ለመስጠት እያንዳንዳቸው ግማሽ ሚሊየን ብር (500,000.00 ብር) ለግሰዋል ፡፡ በአጠቃላይም በዛሬው ዕለት የአንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር (1,500,000.00 ብር) ለኮቪድ – 19 ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ ድጋፍ ተደረጓል ፡፡

ይህንንም በማስመልከት አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ በአደረገው ንግግር “አሁን ጊዜው የማትረፍ ሳይሆን የመትረፍ ነው ፡፡ የሁላችንም ደህንነት ተጠብቆ መቀጠል ስላለብን የዚህን የሀገረ አቀፉን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የበኩላችንን ለመደገፍ ይህን አድርገናል” ብልዋል፡፡ ይህ ዛሬ በታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ የተደረገውን ድጋፍ የኮቪድ – 19 ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ ወክለው የተገኙት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በአደረጉ ንግግር “ሃይሌ ሁሌም በብዙ ነገር ቀዳሚ ነው፣ ይህን በሃገር አቀፍ ደረጃ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለተቋቋመው ኮሚቴ የመጀመሪያው በድርጅት ስም የተሰጠ ድጋፍ ነው ስለዚህም ብዞዎችን ያነቃቃልናል ፡፡ ይህን ጊዜ ተደጋግፈን ማለፍ አለብን” ብለዋል ፡፡ የማራቶት ሞተርስ ኢንጅነሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መልካሙ አሰፋ በዚህ ላይ በመጨመር “ይህን ድጋፍ ያረግነው በብርሃን ጊዜ ሁሉም ያያል ትልቁ ነገር በጨለማ ወቅት ማየት ነው ምክንያቱም ጨለማ ይነጋል፤ ይህንንም ድጋፍ ህብረተሰባችንን ያግዘዋል ብለን ነው ፤ ምህረት ግን ከአምላክ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ትልልቅ የሚባሉት አለም አቀፍ ውድድሮችን ፤ የለንደን ፤ የፓሪስ እንዲሁም የቦስተንና ታዋቂው የደቡብ አፍሪካ ቱኦሽን ማራቶን ጨምሮ ሌሎችንም በርካታ ውድድሮች ለረጅም ጊዜ እንዲተላለፉ ምክንያት የሆነ ሲሆን በዚሁም ሳምንት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ለሚቀጥለው አመት መተላለፉ ታውቋል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዚሁ ዓመት ከሰኔ በፊት ሊያካሂዳቸው ያቀዳቸውን ሁለት ውድድሮች ማለትም ዓመታዊው የአውሮፓ ህብረት የልጆች ሩጫ እኒዲሁም ዘንድሮ ከኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ሰሜን አሜሪካ ጋር በመተባበር በሜኔሶታ ሊያካሂድ የነበረውን ውድድር እንደማያካሂድ ገልጽዋል፡፡

ምንጭ- ታላቁ ሩጫ ፔጅ

 

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team