ተጠባቂው የፕርሚየር ሊጉ ጨዋታ የቀን ለውጥ ተደርጎበታል

 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መሰረት በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአዳማ ከተማ መካከል የካቲት 14 ቀን 2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ ተጠባቂው መርሀ ግብር ነበር ::

 

ሆኖም ግን በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት በመሰቀል አደባባይ ታላቅ የኮንሰርት ዝግጅት ስለሚከናወን እና ሁለቱን አብይት ክንዋኔዎች መምራት የማይቻል በመሆኑ ጨዋታው ሊራዘም መቻሉ ታውቋል ::

ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የከንቲባ ፅ/ቤት እንደተገለፀው በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአዳማ ከተማ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2012ዓ.ም በ10፡00 የሚከናወን ይሆናል፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor