ተጠባቂው የግብፅ ደርቢ በፎርፌ ተጠናቀቀ

ተጠባቂው የግብፅ ደርቢ በፎርፌ ተጠናቀቀ

የግብፅ ተጠባቂው ጨዋታ አልሀሊ የፎርፌ አሸናፊዎች ሆነዋል።

በግብፅ ሊግ እና በአፍሪካ ከሚጠበቁ ታላላቅ ፍልሚያዎች የሆነው የዛማሌክ እን የአል አህሊ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በፈርኦኖቹ ሀገር ዋና ከተማ ካይሮ ላይ የተካሄደ ሲሆን በጨዋታ ዛማሌኮች 30 ደቂቃ አርፍደው በመገኘታቸው የቀኑ አርቢትር ለ አል ቸህሊ 3 ነጥብ እና 3 የንፁህ ጎል በመስጠት የፍፃሜውን ፊሽካ ነፍተዋል።

ከቀናት በፊት የዛማሌኩ ፕሬዝደንት ሞርታዳ መንሱር በቡዳናቸው ተጫዋቾች ላይ የግብፅ እግርኳስ ማህበር በጣለው ቅጣት ምክንያት ከ ሊጉ እራሳቸውን እንደሚያገሉ አስታውቀው ነበር።