መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም በገበያ ላይ ትውላለች፤ አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም በገበያ ላይ ትውላለች፤ አታምልጦት፡፡

አጋራ
አጋራ

ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም በገበያ ላይ
ትውላለች፤ አታምልጦት፡፡
ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው የማክሰኞ እትሟ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ነገ ለእናንተ ውድ አንባቢዎቻችን ልታስነብቦት ከተዘጋጀችው ዘገባዎች መካከል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጠራው አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ ዳግም ውዝግብ ሊፈጠር ይችላል በሚል ስጋት ስለተፈጠረበት ሁኔታ ሰፋ ያለ መረጃን ይዘንላችሁ የምንቀርብ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግንም አስመልክቶ የሊጉን የ22ኛ ሳምንት ጨዋታ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በማድረግ 0-0 ከወጣው የጅማ አባጅፋር ቡድን ተጨዋቾች መካከል ሄኖክ አዱኛንና የወላይታ ድቻን ቡድን 2-0 ከረታው የመቐሌ ከተማ ቡድን ተጨዋቾች መካከል አመለ ሚሊኪያስን በቡድናቸው የሊጉ ጉዞና ስለሊጉ ፉክክር ጥያቄዎችን አንስተንላቸው ምላሽን ሰጥተዋል፤ ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌሎችንም መረጃዎች ለእናንተ ይዛላችሁ ቀርባለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ሌላው በየሳምንቱ ከምታስነብቦት ውስጥ የቀድሞ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዷ ነገ ይዛው የምትቀርበው ተጨዋች በክለብ ደረጃ ከቅ/ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን በመጫወት ያሳለፈውን ድንቁን የአማካይና የቀኝ መስመር የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች ሚሊሻ ጎዳናን ሲሆን ለተጨዋቹ ላቀረብንለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቶናል፤ ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ የነገው ዘገባዋም ልታስነብቦት ከተዘጋጀችው ውስጥ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ነገና ረቡዕ ምሽት በጉጉት ከሚጠበቁት ግጥሚያዎች መካከል ሪያል ማድሪድ ከባየር ሙኒክ ሮማ ከሊቨርፑል የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክቶ መረጃን አቅርበንሎታል፤ ከእዚያ ውጪም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ በማንቸስተር ዩናይትድና አርሰናል መካከል በተደረገው ጨዋታ ዙሪያ ማንቸስተር ባለድል ሲሆን ወሳኙን ጎል ስላስቆጠረው ፌላይኒ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪውኖ የሰጡት አስተያየት ያለ ሲሆን ሌላው ደግሞ የሊቨርፑልን ክለብ ለታላቅ ስኬት እያበቃው ስላለው የመሐመድ ሳላህ የማያቋጥ የኳስ እድገትም የሚወዱት መረጃ ቀርቦሎታል፤ ሀትሪክ ሌላው የምታስነብቦት ጣፋጭ ዘገባ ለባርሴሎና እና ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ለበርካታ ዓመታት ኳስን በድንቅ ብቃቱ በመጫወት ጉዞው ስለተጠናቀቀው አንድሬስ ኢንዬስታም ሊያነቡት የሚጓጉት መረጃ ቀርቦሎታል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት የእኛ ብቻ ሳትሆን የእርሶም ናትና አንብቧት፤

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...