ተወዳጅዋና የመጀመሪያዋ ባለቀለም የሆነችው ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ በአንባቢያን ተደጋጋሚ ጥያቄ በቀጣይ ሳምንት ለንባብ ልትበቃ ነው።

ተወዳጅዋና የመጀመሪያዋ ባለቀለም የሆነችው ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ በአንባቢያን ተደጋጋሚ ጥያቄ በቀጣይ ሳምንት ለንባብ ልትበቃ ነው።
ሀገራችንን ጨምሮ መላው አለምን ባስጨነቀውና በሞት በነጠቀው ክፉ ወረረሽኝ ምክንያት ለሳምንታት ከተከበሩ አንባቢዎቿ ተለያይታ የቆየችው ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ በርካታ የሀትሪክ ቤተሰቦችና ስፖርት አፍቃሪያን በስልክ፣በfb፣በቴሌግራም፣በኢሜልና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ሀትረክ ጋዜጣ ወደ ገበያ እንድትመለስ በተደጋጋሚ በጠየቃችሁት መሠረት በቀጣይ ሳምንት በልዩ ዝግጅት መቅረብዋን የምናበስረው ከምንወዳቸው አንባቢዎቻችን ጋር ለመገናኘት ባለን ከፍተኛ ጉጉትና በከፍተኛ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆነን ነው።
በዚህ አጋጣሚ በፍፁም የተቆርቋሪነትና በባለቤትነትና ስሜት ጋዜጣዋ ወደ ገበያ እንድትመለስ ፍላጎት ላሳያችሁን ያላችሁን ክብርና ፍቅር ለገለፃችሁልን በመሉ ክብረት ይስጥልን እያልን፤በቀጣይ ሳምንት እንደምንገናኝ ቃል እንገባለን።እግዚአብሔር በአለማችንና በሀገራችን ላይ ያንዣበበውን ክፉ ደመና ገፎልን ንፁህ የሰላም አየር ለመተንፈስ ያብቃን።
የሀትሪክ ጋዜጣ ኤዲቶሪያል

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team