በሚቀጥሉት ወራት የምስራቅ አፍሪካ መካለኛው አፍሪካ ውድድር እና 2020 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማጣርያ ሚጠብቃቸው ሉሲዋቹ በብርሀኑ ግዛው ይመራሉ።
በሰላም ዘርአይ እየተመሩ የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻሉት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በሴቶች እግር ኳስ ብዙ ዓመት የሰራውና ውጤታማ ጊዜያትን ያሳለፈው ብርሀኑ ግዛው እየተመሩ በቅርብ ቀናት በታንዛንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በኢኳቶሪያል ጊኒ አስተኛጋጅነት በተካሄደው የ2012 አፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ የቻለው ብርሀኑ ግዛው በቀጣይ ሉሲዎቹን ለ2020 አፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ሀላፊነት ይጠብቀዋል።
አስተያየት ይስጡ