መነሻ ገጽ ሪፖርት ብላቴናው ወላይታ ድቻ ምሽቱን በግብፅ ካይሮ ነግሶ አምሽቷል
ሪፖርትአፍሪካኮንፌድሬሽን ካፕወላይታ ድቻዜናዎች

ብላቴናው ወላይታ ድቻ ምሽቱን በግብፅ ካይሮ ነግሶ አምሽቷል

አጋራ
አጋራ

ወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌደሬሺን ካፕ የመልስ ጨዋታ በግብፅ አልሰላም ስታዲዬም የአፍሪካውን ስመ ገናና ክለብ የግብፁን ዛማሌክ በመለያ ምት በመርታት አዲስ ታሪክ ፅፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ምስጋና ለወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ይድረስ ታሪክ የማይዘነጋው በኢትዮጵያውያን ልብ እስከወዲያኛው ታትሞ የሚኖር በወርቅ መዝገብና ብዕር አዲስ ታሪክ አፅፏል፡፡



በአፍሪካ ኮንፌዴሬሺን ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ወክሎ በመሳተፍ ላይ ያላው ብላቴናው ወላይታ ድቻ የአፍሪካውን ሃያል ክለብ የግብፁን ዛማሌክ በሜዳው በመለያ ምት 4ለ3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ አዲስ ገድል ፅፏል፡፡ወላይታ ድቻ  ትናንት ምሽቱን ነፋሻማ በነበረው የግብፅ ካይሮ የአየር ሁኔታ ዛማሌክን በሜዳው በአልሰላም ስታዲዬም በገጠመበት የኮንፌደሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ በመለያ ምት በማሸነፍ ለስፖርት ቤተሰቡ የገባውን ቃልኪዳን ታማኝነቱንና ቃሉን የጠበቀበትን ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል፡፡

የዛማሌክና ወላይታ ድቻ የመልስ ጨዋታ ትናንት ምሺት በግብፅ 12:00 በኢትዮጵያ 1:00 ሲል በግብፅ ካይሮ አልሰላም ስታዲዬም በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ደጋፊዎች ወደ ስታዲዬም እንዳይገቡ በተጣለው ገደብ ምክንያት ከ4ሺ የማይበልጥ ተመልካች ታጂቦ በጀመረው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ዛማሌኮች በሀዋሳው ጨዋታ 2ለ1 ከተሸነፉበት የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች የ4 ተጨዋቾች ለውጥ በማድረግ ሲገቡ፡ወላይታ ድቻ በሜዳው በሀዋሳ ስታዲዬም ዛማሌክን  2ለ1 ካሸነፈበት ስብስብ ከመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች የአንድ ተጨዋቾች ብቻ ለውጥ ሲያደርግ በዘላለም እያሱ አምረላ ደልታታን ቀይረው በማስገባት ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡

 ኬኒያዊው ዴቪስ አምዊኖ በመሩት የምሺቱ ጨዋታ ዛማሌክ በ4 2 3 1 ፎርሜሺን  ወደ ሜዳ ሲገባ ዲቻ በ4 3 3 ፎርሜሽን ወደ ሜዳ ገብቷል፡፡ጨዋታው  በባለሜዳዎቹ ዛማሌኮች የተጀመረ ሲሆን የመጀመሪያውን  ሙከራ ገና በጨዋታው መጀመሪያ በ1ኛው ደቂቃ በግራ መስመር ሰብረው በመግባት  አስደንጋጭ ሙከራ በማድረግ ቀዳሚም እነሱ ነበሩ፡፡በጨዋታው ወላይታ ድቻ ወደ ሇላ በራሳቸው ግብ ክልል ተጠግተው ሲጫዎቱ ባለሜዳዎቹ ጦረኞቹ ተጭነው ለመጫወት ጥረት ሲያደርጉ ነበር ፡፡በዚህም በድጋሚ በ3ኛው ደቂቃ በቀኝ መስመር በኩል በመግባት በመሀመድ አብዱልጋኒ አማካኝነት ሌላ የጎል ማግባት ሙከራ ሲያደርጉ ድቻዎች ምላሺ ለመስጠት በሞከሩበት እንቅስቃሴ የመጀመሪያውን የማዕዘን ምት ባገኙበት 4′ የመጀመሪያውን ሙከራ ማድረግ ችለዋል፡፡

በሁለቱም በኩል ኳሱን ተቆጣጥሮ ለመጫወት በሞከሩበት በዚሁ የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ባለሜዳዎቹ የጨዋታ የበላይነት ነበራቸው ፡፡በ7ኛው ደቂቃ በመሀመድ አብዱላዚዝ ለግብ የተቃረበ ሙከራ ሲያደርጉ የዲቻው ግብ ጠባቂ ወንደሰን ገረመው በድንቅ ሁኔታ ሲያመክንበት በ8ኛው ደቂቃ በአህመድ ማግቡኒ የግንባር ኳስ አማካኝነት ለትንሺ በግቡ ቋሚ  የወጣች ሌላ የግብ ሙከራ አድርገዋል፡በተደጋጋሚ በግራ እና ቀኝ መስመር በኩል በመግባት የግብ ዕድል በመፍጠር የተሻሉ የነበሩት ዛማሌኮች ቢሆኑም፡ንቦቹ የሚቀመሱ አልነበሩም፡፡ በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ሽግግር በጃኮና በበዛብህ አማካኝነት የዛማሌክ የተከላካይ መስመር ሲረበሹ አምሽተዋል፡፡

በጨዋታው ሂደት በ27ደቂቃ የድቻው አምረላ ደልታታ ተጎድቶ ሜዳ ውስጥ በወደቀበት ቅፅበት የዛማሌኩ መሀመድ አብዱላዚዝ  ልጁን ጎትቶ ከሜዳ ያወጣበት ቅፅበት ፍፁም እግርኳሳዊ ያልሆነ ድርጊት በቢጫ ካርድ ታልፏል፡፡በጨዋታው ሂደት ዛማሌክ በሙከራ የተሻለ ሲሆን በ30,32,40 ኛዎቹ ደቂቃዎች ለግብ የተቃረቡ ሙከራዎች ሲያደርጉ ዲቻ በጥብቅ መከላከል የተሻሉ ሁነው ባመሹበት ታሪካዊ ምሺት በ44ኛው ደቂቃ በቀኝ መስመር በኩል ሳጥኑ ውስጥ ተስፉ ኤሊያስ በጀርባው የነካውን ኳስ የመሃል ዳኛው ለዛማሌክ ፍፁም ቅጣት ምት መስጠታቸው አከርካሪም አነጋጋሪም ሆኖ ግቧን አህመድ አሀታቦሊ በማስቆጠር ዛማሌክን መሪ አደረገ፡፡

ጎሏ የዛማሌክን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድል ከፍ ስታደርግ የዲቻን ተነሰሺነት የድቻን ህልም ያጨለመች ጎል ሁና ስትመዘገብ የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሺ ተጠናቆ ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ዲቻ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የግድ ግብ ማስቆጠር ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ይህን ለማድረግ ወደ ሜዳ የገቡት የጦና ንቦች  በ47ኛው ደቂቃ ሌላ ግብ አስተናግደው በዛማሌክ 2ለ0 መመራታቸው ቀጥሏል፡፡አሁን ሁሉም ነገር ወደ ዛማሌክ ያጋደለ ይመስል ነበር፡፡ዲቻዎች ሌላ ጫና ውስጥም ገብተው በነፋሻማው ምሺት ታሪክ ለመፃፍ ወደ ዛማሌክ የግብ ክልል በተደጋጋሚ በመጠጋት ጎል ለማስቆጠር ፍልሚያው ቀጥሏል፡፡
ድቻዎች የማይቻል የሚመስለውን ችለው በ52ኛው ደቂቃ በአብዱልሰመድ አሊ  ድንቅ የጭንቅላት ኳስ ግብ በማስቆጠር ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ህልማቸውን ያለመለሙበት የግብፅን ሰማይ ያጠቆሩበት ግብ አስቆጠሩ፡፡ጨዋታው በዛማሌክ 2ለ1 መሪነት ቀጥሏል፡፡ዲቻ በሜዳው ዛማሌክን ባሸነፈበት ጨዋታ ያስቆጠሯቸው 2 ግቦች  ሌላ ታሪክ ሊፅፉ ስንቅ ሁነው ንቦቹ የበለጠ እንዲቀስሙ ጉልበት ሆኗቸዋል፡፡

በጨዋታው ባለሜዳዎቹ ነጮቹ ጦረኞች የኳስ የበላይነት በመውሰድ ግብ ለማስቆጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን በማድረግ ብልጫ ቢወስዱም ንቦቹ አጠፋውን ለመመለስ የሚያደርጉት የግብ ሙከራ ተስፋ የሚያጭር ነበር፡፡የጦረኞቹ ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎች በግቡ አግዳሚ ወደ ላይ ለትንሺ ይወጡ ነበር፡፡ድቻዎች በተረጋጋና በተደራጀ ድንቅ መከላከል ግባቸውን ዳግም ላለማስደፈር የዛማሌክን አጥቂዎች ሲናደፉ ዳኛው ቅጣት ምት በመስጠት ሲያመሹ የዕለቱ ጨዋታ በዛማሌክ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ወላይታ ዲቻ ሀዋሳ ላይ ዛማሌክን 2ለ1 በማሸነፉ ድምር ውጤት ዛማሌክ 3 -3 ድቻ=ወደ መለያ ምት አመሩ፡፡
ሁሉም ጫና ውስጥ ገብቷል የመጀመሪያውን መለያ ምት ዛማሌኮች አስቆጠሩ፡፡አሁን ድቻ የመጀመሪያውን መለያ ምት በጃኮ አማካኝነት ለምታት ከዛማሌኩ ግብ ጠባቂ አህመድ ኤል ሼላዊ ጋር ተፋጧል፡፡ጃኮ አስቆጠረ፡፡ ዛማሌክ በተከታታይ ሶስት መለያ ምቶችን ሲያስቆጥሩ ንቦቹም በተመሳሳይ 3ቱንም አስቆጠሩ፡፡ዛማሌክ 4ኛውን መለያ ምት አመከኑ የዲቻው ተክሉ አስቆጠረ የግብፅ ሰማይ እስከወዲያኛው አጨለመ፡፡ጦረኞቹ ሌላኛውን መለያ ምት ተመለሰባቸው ፡አላስቆጠሩትም ፡ለግብፃዊያን ህልም በሚመስል የጨዋታ ውጤት በብላቴናው ዲቻ ተሸንፈው በነፋሻማው አየር በጥቁሩ ሰማይ ስር በሚያንዣብበው ዳመና ሀዘን እየተርከፈከፈባቸው አምሽተዋል፡፡ጨዋታው በዲቻ 4ለ3 ተጠናቋል፡፡መለያምቶቹን፡ጃኮ፡አይመን፡አብዱልዘመድና፡ተክሉ አስቆጠሩ ዛማሌክ በብላቴናው ዲቻ በሜዳው ተሸንፎ ከውድድሩ ወጥቷል፡፡ምሽቱ  በግብፅ መሪር ሁኗል፡፡

☞ትንሹ |ብላቴናው|ህፃኑ| ወላይታ ድቻ 

• ድቻ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትንሳኤና ምልክት ሁኖ አምሽቷል፡:

•ድቻ ለክለቦቻችን የትልቅ መነቃቂያ ስንቅ ሁኖ አምሽቷል፡፡

•ዲቻ የማይሞከር የሚመስለውን ሞክሮ የማይቻል የሚመስለውን ችሎ የማይቻል ነገር አለመኖሩን አሳይቷል፡፡

•ድቻ እራሱን በታሪክ ድርሳን አፅፏል፡፡

• ድቻ ታሪካችን መልሷል፡፡
ብላቴናው ወላይታ ድቻ አሁን  የታላላቅ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል፡፡ወላይታ ድቻን የማያውቁት የስፓርት ባለሙያዎችም ሆኑ ጋዜጦች አልያም የመገናኛ ብዙሃን ይህንኑ ብላቴና ወላይታ ድቻን ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ጋዜጦች የጦና ንቦቹን በፊት ገፃቸው ይዘው ለመውጣት ጥድፊያ ውስጥ
ናቸው፡፡የኢለክትሮኒክስ ሚዲያው በስፖርት ዘርፍ ማለቴ ነው ማጠንጠኛው ይሄው ብላቴና ወላይታ ድቻ ነው፡፡የሚዲያ የካሜራ ሌንሶች ሙሉ ለሙሉ ወላይታ ድቻ ላይ ትኩረታቸውን አድርገው አምሽተዋል፡፡

የአሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ አስተያየት -ከግብፅ ካይሮ 

☞”ዛሬ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ሜዳ ላይ በነበረው እንቅስቃሴ ደስተኛ ባልሆንም ውጤቱ ግን አስደስቶኛል፡፡በጨዋታው ላይ መከላከል ላይ አመዝነን ተጫውተናል፡፡ይሄ ግን የኔ ትዕዛዝ አልነበረም፡፡የኔ ትዕዛዝ አጥቅተን በመጫወት ተጋጣሚያችን ጫና እንዲያድርበት ከቻልንም ጎል ስለማስቆጠር ነበር የነገርኳቸው፡፡ተጨዋቾቹ ሜዳ ውስጥ ሲገቡ ወደ ሇላ ተመልሰው ሲከላከሉ ነበር፡፡

ይህንንም በመጠኑም ቢሆን በእረፍት ሰዓት ተነጋግረን በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ  ስተቶቻችን ለማረም ሞክረን ግብ   አስቆጥረናል፡፡በጨዋታው በዳኝነት በኩል ጫና ተደርጎብን ነበር፡፡ድቻ ስንባል ግብፆች አያውቁንም ነበር፡አሁን ግን ማን እንደሆንን አሳይተናቸዋል፡፡የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ፡ድሉ የእናንተ ነው ብለዋል፡፡”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...