ባለዕዳ ክለቦች እየከፈሉ ነው !

 

አዲሱ የሊግ ኮሚቴ የሚጠበቅባቸውን የመመዝገቢያ 780 ሺህ ብር አልከፈሉም በማለት እገዳ ከጣለባቸው 7 ክለቦች መሃል 4ቱ ሰበታ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ስሁል ሽረና ሃዲያ ሆሳዕና በነፍስ ወከፍ የሚጠበቅባቸውን 780ሺ ብር መክፈላቸው ታውቋል፡፡ ከሰባቱ ክለቦች ሁለቱ ወልቂጤ ከተማና ሲዳማ ቡና ከፍለናል ያሉ ሲሆን የመክፈላችሁን ማረጋገጫ አምጡ ተብለው እየተጠበቁ መሆናቸው ተሠምቷል፡፡ ከሰባቱ ክለቦች ዝምታ የመረጠው ጅማ አባጅፋር ሲሆን በዝምታው ከፀና የፊታችን እሁድ ከባህርዳር ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ፎርፌ ሊባል እንደሚችል መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ከ16ኛው ሳምንት 8 ጨዋታዎች ላይካሄድ ይችላል የተባለውም ይሄ ጨዋታ ይመስላል፡፡ ሳይከፈል ሁለቴ ፎርፌ መስጠት ደግሞ ክለቡን ወደታችኛው ሊግ የሚያወርድ ይሆናል፡፡ በጉዳዩ ዙርያ የክለቡን ምላሽ ለመስማት ወደጅማ አባጅፋር ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ጋር ብደውልም ስልኩ አይነሳም ቴክስት አድርጌም ምላሽ አልሰጡኝም፡፡ ክለቡ አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ከግምት በማስገባት አመራሮቹ ፈጣን ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደጋፊዎችም ቢሆኑ ጫና ማሳደር ካለባቸው አሁን ይመስላል፡፡ በተቀመጠ ህግና መመሪያ ዙሪያ ጠንካራ አቋም መያዙንና በዚህ በኩል የማንንም ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማያስተናግድ ከአዲሱ ሊግ ኮሚቴ የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport