መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ባለከለሯና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም በገበያ ላይ ትውላለች በየሳምንቱ ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እናንተ አንባቢዎች የምትወዱትን የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ትቀርባለች፤
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ባለከለሯና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም በገበያ ላይ ትውላለች በየሳምንቱ ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እናንተ አንባቢዎች የምትወዱትን የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ትቀርባለች፤

አጋራ
አጋራ

ባለከለሯና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም
በገበያ ላይ ትውላለች
በየሳምንቱ ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እናንተ አንባቢዎች የምትወዱትን የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ትቀርባለች፤ ሀትሪክ ነገ በሀገር ውስጥ ይዛሎት የምትቀርበው ዘገባ የኢትዮጵያ አርቢትሮችን ማህበር በተመለከተ የማህበሩ አባል የሆነው ፌዴራል አልቢትር አሰፋ ደቦጭ ‘‘በማህበራችን አመራሮች አቋም መሸርሸር ተገርሜያለው፤ ከፌዴሬሽኑ ሰዎች ጋር በትከሻ ሲነካኩብን ነበር” በሚል የሰጠው ቃለ-ምልልስና ሌሎችም ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሹን የሰጠ ሲሆን፤ ከእዚያ ውጪም ሀትሪክ ስፖርት ክልሎች እግር ኳሳችንን የሚጠቅሙ እንጂ ለግል ጥቅማቸው የሚሮጡትን እንዳይወክሉ በሚልም የተሰራ ሰፋ ያለ ዘገባን ይዘንሎት ቀርበናል፤ ስለ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም የአዳማ ከተማው ስኬታማ ተጨዋች ከነሃን ማርክነህ ስለቡድናቸው፤ ዋንጫ ስለማንሳት ዕድላቸውና ሌሎችንም ጥያቄዎች አንስተንለት የሰጠን ምላሽ አለ፤ ሀትሪክ ስፖርት የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምታስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዷም ነገ ይዛሎት የምትቀርበው ተጨዋች የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በክለብ ደረጃ ደግሞ ለጅማ ሕንፃ ኮሌጅ፤ ለአየር ኃይልና ለቅ/ጊዮርጊስ ተጫውቶ ያሳለፈውን ጎላ ብርሃኑን ነው፤ ለጎላ በኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ስላሳለፋቸው በርካታ ጉዳዮች ጥያቄን አቅርበንለት ምላሹን የሰጠን ሲሆን በተለይ በተጨዋችነት ዘመኑ በእነሱ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን ሲመረጡ የደስታው ስሜት ከፍ ያለ እንደነበርና በተለይ ደግሞ የክፍለ ሀገር ልጅ ሆነን ስንመረጥ ደስታው ማስትሬት ያገኘ ሰው ያህልም ነው የምንደሰተውም ብሎም የሰጠው ምላሽም ይጠቀሳል፤ የጎላን ሰፋ ያለ ቃለ-ምልልስ በነገው ሀትሪክ ላይ ያገኙታል፤ ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትም የህር ማዶ ዘገባዎቿም ይዛሎት ከምትቀርበው ውስጥ ‘‘የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ካነሳን ዓመቱ ስኬታማ ይሆንልናል” በሚል የማንቸስተር ዩናይትዱ ማርኮስ ራሽፎርድ የሰጠው አስተያየት ያለ ሲሆን ከአርሰናል ጋር በተያያዘም የቬንገር ቁጭት፣ የዴይን መልቀቅና ከሀይብሪ ወደ ኤምሬትስ ስለተደረገው ሽግግርም ሰፋ ያለ መረጃ ቀርቧል፤ ሊቨርፑልን አስመልክቶም በቻምፒዮንስ ሊግ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለበትን ጨዋታ ተንተርሶም ከኤልክላሲኮው ግጥሚያ ሊቨርፑል ምን ይማራል በሚለው ላይም የሚወዱት ዘገባ ቀርቧል፤ ሌሎችንም የባህር ማዶ ዘገባዎች ሀትሪክ ይዛሎት ወጥታለች ነገ ያንብቧት፤ አታምልጦት፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...