ባለቀለሟ፣ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ የማክሰኞ እትም ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ከእጃችሁ ትደርሳለች፤ ለመሆኑ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን? ከሀገር ውስጥ፡- ሀትሪክ ስፖርት የፊታችን እሁድ የመጋበዝ እድል ስላገኘችበትና በስፍራው በመገኘትም ስለምትታደምበት የኦቷዋ ማራቶን ሰፋ ባለ መልኩ ዘገባን ይዘን የቀረብን ሲሆን ውድድሩን አስመልክቶም ተወዳዳሪ ከሆኑት አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነውን አትሌት የማነ ፀጋዬን አናግረነው ስለ ውድድሩ ምላሹን ሰጥቷል፤ ከእዚህ ዘገባ ውጪም በቅርቡ የመከላከያና የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ክለቦች ያደረጉት ጨዋታ ላይ የዕለቱ አልቢትር እያሱ ፈንቴ በመደብደባቸው ምክንያት ጨዋታው ከተቋረጠ በኋላ ከእሳቸው ጋር በተያያዘ እየወጣ ስላለው መረጃና ከዳኝነቱም ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አልቢትሩ ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የሰጡት ቃለ-ምልልስ ስላለ እሱንም አቅርበንላችኋል፤ ሀትሪክ ስፖርት ከእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ምርጫ ጋር በተያያዘም የምትሰጦት መረጃ አለ፤ ከእዛ ውጪም የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ ዓምዳችን ነገ ይዘንላችሁ የምንቀርበው ተጨዋች በተጨዋችነት ዘመኑ ለሕንፃ፤ ለመድን፣ ለኢትዮጵያ ቡና፣ ለኒያላ፣ ለጉና፣ ለሐዋሳ ከነማ ለትራንስ ኢትዮጵያና የብሔራዊ ቡድን ውስጥም ተመርጦ የነበረውን ግብ ጠባቂው ጥላሁን እሸቱን /አክሮባትቲስቱን ግብ ጠባቂ ሲሆን/ ከእሱ ጋርም በእግር ኳስ ሕይወቱ ዙሪያ ሰፋ ያለ ቆይታን አድርገናል፤ ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በዋናነት እናንተን ልታስነብቦት የተዘጋጀችበት ሰፋ ያለው ዘገባ በሊቨርፑልና በሪያል ማድሪድ መካከል የፊታችን ቅዳሜ በኪዬቭ ከተማ ፍፃሜውን በሚያደርገው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዙሪያ ሲሆን የሚወዱት ዘገባ ተሰርቷል፤ ሌሎች የባህር ማዶ ዘገባዎችንም ሀትሪክ ይዛለች፤ አታምልጦት፡፡
የነገው የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ /ምስል/ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ